የነጻነት ታጋዩን ገድለዉ በሞቱ - TopicsExpress



          

የነጻነት ታጋዩን ገድለዉ በሞቱ የተሳለቁት ዋጋ የሚከፍሉበት ቀን ይመጣል። ነሃሴ 24 ቀን 2013 የነጻነትና የእኩልነት መብቶች ታጋይ የኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳን ዜና እረፍት ከተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ ተለቆ ባነበብኩ ጊዜ የተሰማኝን የሀዘን ስሜት በቃላት ለመግለጽ ያስቸግረኛል። የመብት ታጋዩ ታሞ ህክምና በመከልከል በወያኔ መንግስት ጭካኔ በመሞቱ በሃዘን ልቡ ያልደማ የለም። በመላው ኣለም ያሉ ኢትዮዽያውያን ሃዘናቸውን በቁጭት በመግለጽ ነፍሰ ገዳዩን የወያኔ ኣገዛዝ ኣውግዘዋል። እንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ በተማረው ትምህርት ሰርቶ ሃገሩን እንዳይረዳ በተደረገበት ክትትልና ማሳደድ ምክንያት ከወገኖቹና ከሃገሩ ተለይቶ ወደ ኬኒያ ለመሰደድ የተገደደ ወጣት ባለሙያ ነበር። በኬኒያ መንግስት ትብብር በናይሮቢ ከተማ ከጓኛው እንጂነር መስፍን ኣበበ ጋር ተይዘው በ2007 ወደ እትዮዽያ ተመልሶ በጨካኙ የወያኔ መንግስት እጅ ወደቀ። ኢንጅኔር ተስፋሁን ጨመዳን ዩኒቨርሲቲ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ነው የማውቀው። በ 2008 የጭራቆቹ መሪ በነበረው መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በኣንድ ቀን ከ ኣዲስ ኣበባ ብቻ ወደ መቶ የምንጠጋ የኦሮሞ ተወላጆች ከየበታችንና የስራ ቦታችን ታፍነን በታሰርንበት ወቅት ደግሞ በማእከላዊ ከዚያም ቃልቲ ዛሬ ህይዎቱ ያለፈችበት እስር ቤት ኣብሬ ነበርኩ። ማእከላዊ ተገናኝቶ መነጋገር ቀርቶ በሩቅ መተያየትም ወንጀል ስለሆነ ከሩቅ ከመተያየት ውጭ ተነጋግረን ኣናውቅም።ቃልቲ ኣብረን በነበርን ጊዜ ግን እድል ኣግኝተን ለመንጋገር ችለን ነበር። ተስፋሁን ከጓደኛው መስፍን ኣበበ ጋር የተያዙት በኬንያ የጸረ ሽብር ፖሊሶችና በኣሜርካ ኣፍቢኣይ(FBI) ጋር እንደነበርና እነሱም ኣስፈላጊውን ምርመራ ካደረጉ በኋላ ከሽብር ጋር ምንም ግንኙነት እንዳልነበራቸው ኣጣርተው ለቀቁዋቸው። ወዲያውኑ በሌሎች የኬንያ ፖሊሶችና በወያኔ ሰላዮች እንደተያዙና ማንም ጉዳያቸውን እንዳይከታተል ከናይሮቢ ከተማ ወዳልታወቀ ኣካባቢ ወስደው በጨለማ ቤት ውስጥ እንዳሰሩዋቸው ነግሮኛል። ከዚያም ሌላ ቀን በሌሊት ወስድው ወደ ኢትዮዽያ እንደመለሱዋቸው ሁለቱም ማለት መስፍንና ተስፋሁን ኣጫውተውኛል። ኢትዮዽያም እንደደረሱ በአዲስ ኣበባ የግል መኖሪያ ቤት በሚመስል በምድር ቤት በጨለማ ውስጥ ከኣንድ ኣመት በላይ ለሆነ ጊዜ ጸሃይ ሳያዩ ታስረው ሲደበደቡና ሲሰቃዩ እንደነበር የደረሰባቸውም በደል ተወዳዳሪ እንደሌለው ይናገሩ ነበር። ተስፋሁን እጅግ ሲበዛ ጨዋና ረጋ ያለ ለሰው ልጆች ሁሉ መልካሙን የሚምኝና ጭቆና ተወግዶ ሁሉም ህዝቦች በሰላም በመፈቃቀድና በመከባበር በገዛ ሃገራቸው ያለ ስጋት በነጻነት እንድኖሩ የሚመኝ ኣርቆ ኣሳቢ የነጻነት ታጋይ ነበር። ተስፋሁን ብዙ ማንበብ የሚወድ በመሆኑ ገና በወጣትነት እድሜዉ የጠለቀ እውቀት ነበረው። የወያኔ መንግስት የኦሮሞ በሄርተኞችን ተከታትሎ ለማጥፋት በ 1989 ኣመተ ምህረት ህዝባዊ ኣደራ በተባለው መጽሄት ያሰፈረውን የኦሮሞ የመብት ትግል ደጋፊ ድርጅት ( Oromiya support group (OSG) ) እንደሚከተለው በሪፖርቱ ላይ ኣስፍሮኣል። ’’To defend narrow nationalism……….must be part of our struggle. In order to have a lasting solution to our problem ……….we have to break narrow nationalist tendencies in Oromia….. we have to fight narrow nationalism to the bitter end……….. to smash it in a very decisive manner ….. fighting the higher intelectual and bourgeois classes in a very extensive and resolut manner …… the standard bearers of narrow nationalism are the educated elite and bourgeoisi. We must be in a position to irradicate all narrow nationalists…….’’ በዚህ መንግስታዊ ፖሊሲ መሰረት በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ወጣቶችን፣ ኣርትሶቶችን፣ በህዝባቸው ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ኣዛውንቶችንና ሴቶችን ጭምር ገድሏል። በፖሊሲው ላይ በተገለጸው መሰረትም በተለይም በተማሩ የኦሮሞ ወጣቶች ላይ በማነጣጠር ኣድኖ ገድሏል። የኢንጂነር ተስፋሁን ግዲያም የዚያ ፖሊሲ ቀጣይ የወያኔ እርምጃ ነው። ኢንጅነር ተስፋሁን ጨመዳ ረጅም እቅድና ህልም የነበረው ቢሆንም በጭካኔኣቸው ወደር በሌላቸው ጭራቆች እጅ ህይዎቱን ኣጥቷል። ተስፋሁን በኣካል ሞተ እንጂ ታሪኩ ኣይሞትም። እንደሱ በርካቶች በዚሁ ጨካኝና ኣረመኔ ቡድን ተግድለዋል። የነጻነትና የመብት ታጋዮች ቢሞቱም ትግል ኣይሞትም። ተስፋሁን የተገደለው መሳሪያ ኣንስቶ መንግስትን ኣልተዋጋም። የተገደለው ለነጻነት በሰጠው ዋጋ ጭቆናን የማይቀበል ሆኖ በመገኘቱ ነው። ኢንጅነር ተስፋሁን ወደር በሌለው ጭካኔ ተግድሏል። ገዳዮቹም በደስታ መፈንደቃቸውን ለመደበቅ እንኳን ባልቻሉበት ሁኔታ ገልጸዋል። እንኳን በሰው ልጅ በእንስሳ ወይም ኣውሬ ሞት ከት ብሎ የሚስቅ ሰብዐዊ ፍጡር የለም። ሰብአዊ ፍጡር የሆነ ሁሉ ለሞተ ሰው ሁሉ ባያልቅስም ማዘኑ ኣይቀርም። ይህ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው። የተፈጥሮ ስሜት ነው። የሆነ ሆኖ ውጣቱን የኦሮሞ መብት ኢንጂኔር ተስፋሁን ጨመዳ ታጋይ ህይወት ባጭር የቀጩት የወያኔ ባለስልጣኖች ፍጽም እንስሳዊ በሆነ ሁኔታ ተሳለቁ። ከኢሳት ሬዲዮና ተለቭዥን የታጋዩን ሞት ምክንያት ሲጠየቁ ከት ብለው በመሳቅ በእርግጥም ሰብአዊ ፍጡር ኣለመሆናቸውን ኣስመስክረዋል። የኢትዮዽያ ሳቴላይት ሬዲዮና ቴሌቭዥን ባልደረባ ኣቶ ካሳሁን የእንጂኔር ተስፋሁን ጨመዳን በቃልቲ እስር ቤት መሞቱን የሰማ መሆኑን በመግለጽ ምክንያቱን ለማወቅ ባደረገው ሙከራ የሚከተለውን መልስ ኣግኝቷል። ኣቶ ካሳሁን የተስፋሁንን ሞት ምክንያት ለማወቅ በመጀመሪያ ለፈደራል ማረሚያ ቤት ዋና ኣስተዳዳሪ ለተባለው ዴውሎ በስልኩ ላይ የተገኙት ትክክለኛ የሚፈልጋቸው ሰው ለመሆናቸው ለማውቅ ’’ኣቶ ብርሃን ኖት’’ ቢሎ ከጠየቀ በኋላ ኢንጅነር ተስፋሁን የተባለ እስረኛ በቃልቲ እስርቤት መሞቱን ከማህበራዊ ድረገጾች ማወቁን ኣስረድቶ የሞተበትን ምክንያት ለማወቅ ይቻል እንደሆነ በማለት ከአንድ ጋዘጤኛ በሚጠበቅ ስነስርአት ጠየቀ። ኣቶ ብርሃን የተባሉት ግለሰብም ተስፋሁን ኣ ኣ! የሞተበት ምክንያት ’’ኣዎ ይታወቃል እንጂ በሚገባ ይታወቃል’’ የሚል መልስ ስጠ። ጋዘጤኛ ካሳሁንም እስቲ ይንገሩኝ በማለት ምክንያቱን ለማወቅ በጉጉት ሲጠይቅ ኣሁን ዋና መስሪያ ቤት ነው ያለሁት ቃልቲ ማረሚያ ቤት ሆስፕታል ቢደውሉ መረጃውን ያገኛሉ በማለት ’’በሚገባ ኣውቃለሁ’’ ያለው ወደ ሌላ ኣስተላለፈው። ካሳሁንም ወደ ቃልቲ ሆስፕታል ደወለ። ከዚህኛውም የሚገርም መልስ ኣገኘ ሆስፕታሉ ስለተስፋሁን መሞት ምንም መረጃ እንደለሌው ገልጾ የህዝብ ግንኙትን እንዲጠይቅ ነገረውና ኣረፈ። በቃልቲ ማጎሪያ ቤት የህኪምና ኣገልግሎት በማጣት በየቀኑ ህይዎታቸው የሚያልፍ በቀላል ኣይገመትም። እኔ እዚያ በነበርኩ ጊዜ በኣንድ ወር ውስጥ ኣራት ሰዎች ካአንድ ዞን መሞታቸውን ለመታዘብ ችያለው። የሚታመሙ ታሳሪዎች ለሞት እስኪያጣጥሩ ድረስ ማንም ዞር ብሎ ኣያያቸውም። ኣብረው ያሉ ታሳሪዎች ብወተውቱም የሚሰማ የለም። በመጨረሻ እንደማይተርፉ ሲረጋገጥ ተ ወስደው በእስር ቤቱ ክልኒክ ኣጠገብ ባሉት ወና ክፍሎች ውስጥ ይጣላሉ ክዚያም ህይዎታቸው ካለፈ በኋላ ምኒልክ ሆስፕታል እሬሳቸው ተውስዶ ይጣላል። እንደዚህ ኣይነት ወራዳ ስራ የሚሰሩ የሆስፕታል ሰዎች ናቸው እንግዲህ የወጣቱን መሞት ሆስፕታሉ መረጃ የለውም ቢለው የሚያፌዙት። ካሳሁን ኣሁንም ተስፋ ኣልቆረጠም በተሰጠው ስልክ ቁጥር ኣቶ ግዛቸው መንግስቱ የተባለውን የህዝብ ግንኙነት ተበዬውን ስለ ተስፋሁን ጨመዳ በቃልቲ እስር ቤት ህይዎት ማለፍ ኣስረድቶ ምክንያቱን ጠየቀው። ኣውሬው ግዛቸውም ከት ቢሎ ከሳቀ በኋላ ’’ሌላስ’?’ ኣለ። ካሳሁንም ይህንኑ ይንገሩኝ በማለት መልሱን ሲጠብቅ ግለሰቡ ኣሁንም እየሳቀ ’’በህመም ነው የሞተው የህኪምና ባለሙያ ነው የሚያውቀው’’ በማለት ኣፌዘ። ጋዘጤኛ ካሳሁንም በዋዛ ኣላለፈውም ጉዳዩ ኣሳሳቢ ነውና ሰው ሞቶ መሳቁ ተገቢ ነው ይላሉ በማለት ግለሰቡ ምን ያህል ደደብ እንደሆነ ኣጋለጠው። ኣውሬው ግዛቸውም በዚሁ ስልኩን ዘጋበት ለዚህም ኢሳትን በተልይም ኣቶ ካሳሁንን ከልብ ላመሰግን እወዳላሁ ለወደፊቱም እንደዚሁ የሙያ ግዴታችሁን ለመወጣት በርቱ እላለሁ። ይህን እጅግ የወረደ የግዛቸው ድርጊት በተስፋሁን ላይ ብቻ የተፈጸመ ኣይደለም። ይህ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ብቻም የተፈጸመ ኣይደለም። ይህ ከማንኛውም የወያኔ መንግስት የግፍ ስራዎች በእጅጉ የላቀ ንቀት ከኢትዮዽያ ህዝቦችም ኣልፎ በስው ዘር ላይ ማ ፌዜ ነው ። ይህ ድርጊት ተስፋሁንን በወ ለደችው እናት ላይ ብቻ የተሳቀ ነው ብሎ መውሰድ ኣይቻልም በመላው የኢትዮ ዽያ እናቶች ላይ ነው የተቀለደው። የወያኔ ኣራዊት ጭቅላ ህጻን በእናት ጀርባ ላይ እንደ እባብ በዱላ ቀጥቅጠው እንደገደሉ ባለፈው ሰምተናል ። እነዚህን በምን ቃላት መግለጽ ይቻላል? የወያኔ ባለስልጥናት ጭራሽ ሞራል ከሚባል የሰው ልጅ ባህሪይ ጋር የማይተዋወቁ ከጫካ ኣውሬም በታች መሆናቸውን በግልጽ ያወጁበትና ከምን ጊዜውም በበለጠ ያጋለጡበት ድርጊት ነው። እነዚህ ከእንስሳ በታች የሆኑ ነፍሰ ገዳዮች በምንም መልኩ ቸል ሊባሉ የማይገባ ነው። እነዚህ ጭራቆች የሰውን ስጋ ከመብላት ወደኋላ የማይመለሱ የቀን ጅቦች እስከመቸ ድረስ ትውልድን እየበሉ ይኖራሉ? እነዚህ ባህል ኣልባ የሆኑ ሞራለብሶች በኣስቸኳይ ካልተወገዱ ሰላምም ሆነ ጤና ሊኖረን ኣይችልም። ኤረጎበዝ እየጨረሱን ሲስቁብንና ሲያፌዙብን እስከመቼ ልንታገሳቸው ነው? የወያኔ ባለስልጣናት ቁንጮኣቸው ከነበረው ሟቹ መለስ ዜናዊ ጀምሮ ባለፉት ሃያ ሁለት ኣመታት ስገሉን፣ ሲያስሩን፣ ከሃገር ሲያስውጡን ይሄው ከዚያም ኣልፈው ገድለውን ሲስቁብን ኣይተናል እያየንም ነው። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ማን ነው ብለን እራሳችንን መጠቅ ኣለብን። የእነዚህ ኣውሬዎች ድርጊት በዚህ የሚያቆም ስላልሆነ መፍትሔ የሚሻ ጉዳይ ነው። ያገባናል የምንል ሁሉ ተቀራርበን መወያየት ኣለብን። ይህ ካልሆነ አላይ እንደተመለከትነው ባስቀመጡት እቅድ መሰረት የሃገሪቷን የነገ ተስፋ ትውልድ ሁሉ ከመፍጀት ኣይመለሱም። የወያኔ መንግስት የነቁና ለህዝቦቻቸው ነጻነትና ክብር የሚታገሉትን ከማጥፋት ወደ ኋላ እንደማይል ባግልጽ እያየን ነው። እነ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ ኣንዱኣለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለምን ወንጀል ተይዘው የተፈረደባቸውም የእቅዱ አካል መሆኑን ለመረዳት ኣያዳግትም። የዚህ ቡድን እስትራቴጅ በጥይት መግደል ሳይሆን ለዚሁ ባዘጋጀው የጸረ ሺብር ህግ ይዞ በማሰርና በቅጥረኛቹ ዳኞች አማካይነት የሞትና የእድሜ ልክ በማስፈረድ በእስር ቤት እንዲያልቁ ማድረግ ነው። ይህ ጉዳይ በጣሙን ሊያሳስበን ይገባል። ተስፋሁንንም ሆነ ሌሎችን የገደሉ። ያሰሩና ያሰቃዩ፣ ገድለው ያፌዙ ሁሉ የሚጥየቁበት ቀን ይመጣል፣ በቀለ ከስውዲን ኢትዮሚድያ - Ethiomedia September 1, 2013
Posted on: Tue, 03 Sep 2013 13:44:39 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015