የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ሳዑዲ አረቢያ - TopicsExpress



          

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ሳዑዲ አረቢያ ገባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ የሚመራ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን የያዘ የልኡካን ቡድን ለስራ ጉብኝት ሳዑዲ አረቢያ ገባ፡፡ የሳዑዲ አረቢያ የአሹራ ምክር ቤት ባደረገለት ግብዣ መሰረት ወደ ሳኡዲ ያቀናው የልኡካን ቡድን በሀገራቱ ምክር ቤቶች የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ የመግባቢያ ሰነዶችን ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያ የአሹራ ምክር ቤት አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ሚህሲን ቢን ዓሊ ፋሪስ አል ሀዚኒይ ለልኡካን ቡድኑ አቀባበል አድርገውለታል፡፡ ጉብኝቱም በሁለቱ ምክር ቤቶች መካከል የተጀመረው የሁለትዮሽ ግንኙነት በተጠናከረ መልኩ በሚቀጥልበት መንገድ ላይ በመምከረ ከስምምነት ለመድረስ ያለመ ነው፡፡ አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዳሉት በሳኡዲ ዓረቢያና በኢትዮጵያ መካከል ረጅም እድሜ ያስቆጠረ መልካም ግንኙነት በዚህ ወቅትም በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ ሳኡዲ ዓረቢያ የሰራተኛ ሀይል የምትፈልግ ሀገር እንደመሆኗ ይህንኑ ህጋዊ በሆነ መልኩ በሁለቱ ሀገሮች መካከል በሚደረግ ስምምነት መሰረት ለማከናወን የኢትዮጵያ መንግስት ስራ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ ከሳዑዲ ዓረቢያ ምክር ቤት ጋር ከሚያደርጉት ውይይት በተጓዳኝ በሪያድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየትም እቅድ ይዘዋል፡፡ ምንጭ፦በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ/ኢብኮ
Posted on: Sun, 28 Dec 2014 08:16:29 +0000

Trending Topics




© 2015