የፊደሏ ጣጣ ጎልማሳው ለሥራ ጉዳይ - TopicsExpress



          

የፊደሏ ጣጣ ጎልማሳው ለሥራ ጉዳይ ካለበት ብርዳማ የአሜሪካ ግዛት ወደ ሌላ ሞቃታማ ግዛት ይጓዛል፡፡ ባለቤቱም በቀጣዩ ቀን እንደምትመጣ ተነጋግረው ነበር፡፡ ጎልማሳውም ታዲያ የሆቴል ክፍሉ ውስጥ ሆኖ ለባለቤቱ የኢ- ሜይል መልዕክት ይልክላታል፡፡ ሆኖም ግን አድራሻዋን ሲጽፍ አንዲት ፊደል ይስትና የኢ-ሜይል መልዕክቱ ወደ ባለቤቱ መሄዱ ቀርቶ አቅጣጫውን ስቶ ወደ አንዲት ባለቸው ወደ ሞቱባቸው ባልቴት ዘንድ ይሄዳል፡፡ ሴትዬዋ የሃይማኖት ሰባኪ ባላቸው ከሞቱ ገና አንድ ቀናቸው ነበር፡፡ ሐዘን ላይ ያሉት ባልቴት የኢ-ሜይል መልዕክቶቻቸውን ሲፈትሹ (ቼክ ሲያደርጉ) ይህን መልዕክት ያዩና ይከፍቱታል፡፡ ወዲያው ግን ጮኸው መሬት ላይ ይዘረራሉ፡፡ ልጆቻቸውም ተሯሩጠው መጥተው ሲያዩ እናታቸው መሬት ላይ ወድቀዋል፡፡ በምን ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ ወደ ኮምፒዩተሩ ተጠግተው ተመለከቱ፡፡ ኮምፒዩተሩ ስክሪን ላይ የተጻፈው መልዕክት:- “ውድ ባለቤቴ እኔ ደርሻለሁ፡፡ ይገርምሻል፤ እዚህ በጣም ይሞቃል፡፡ ላንቺም ነገ መምጣት ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶ እየጠበቀሽ ነው! ከልጆችሽ ተለይቶ መምጣቱ እንዳይከብድሽ ! ያንቺው! የሚል ነበር፡፡
Posted on: Wed, 10 Jul 2013 20:31:07 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015