የፊፋ ህግ እንዲህ ይላል..2011 edition art(55) "A - TopicsExpress



          

የፊፋ ህግ እንዲህ ይላል..2011 edition art(55) "A match suspension is regarded as no longer pending if a match is retroactively forfeited becouse a player took part in a match despite being ineligible" ስለዚህ ክሳቸዉ የህግ መሰረትና ተቀባይነት ላይኖረዉ ይችላል:: የደቡብ አፍሪካ ሚዲያዎች ልክ እንደ እንግሊዞች ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ናቸዉ የሀገሪቷን ጥቅም ለማስጠበቅ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ለዚህም ይመስላል አሁን የከፈቱትን ክስ ለማጠናከር ተደጋጋሚ ዘገባዎችን በማዉጣት ላይ ያሉት:: በዛም በዚህም አምታተዉ ለማለፍ እየሞከሩ ነዉ አሁን ትልቅ ፈተና ከፊታችን ይጠብቀናል ፈተናችን የመጨረሻዉ ተጋጣሚያችን ሴንትሪል አፍሪካ ብቻ አይደለችም ካፍም ሆነ FIFA የኢትዮዺያን ማለፍ አይፈልጉትም.. ደ. አፍሪካን ይመርጣሉ:: ሌላዉ ፈተና ራሱ የደ.አፍራካ football ፌደሬሽን ነዉ ተጋጣሚያችንን በገንዘብ በመደገፍ ጭምር ይመጣብናል:: እና ምን ቢደረግ ነዉ መልካም የሚሆነዉ? የእኛን ሚዲያዎችን እንኯን ተዉዋቸዉ ያለ ኢንተርኔት መስራት እንደማይችሉ አሁን ለይቶላቸዋል:: ኢንተርኔት በርብሮ መረጃ መስጠትማ እኛም እንችልበታለን የሀገርን ጥቅም የሚያስከብር ሁነኛ ሚዲያ ጠፋ እንጂ:: ዛሬ ማታ እከሌ የተባለዉ ተጨዋች ምን የመሰሰለ በርገር ስለመብላቱ ጠዋት ከመኝታህ ተነስተህ ቁርስህን እንኯን ሳትበላ የሚነግርህ ጋዜጠኛ..ፐ ፐ አስብሎህ የምግብ ፍላጎትህን የሚያስዘጋ ጋዜጠኛ በሞላባት ኢትዮዺያ ዛሬ ሚሊዮናች ደስታ ላይ ተቀለደ:: አሁንም ደግሜ እላችሁዋለሁ እነዚህ ሰዎች መቀጠል በተዕምር የለባቸዉም
Posted on: Wed, 19 Jun 2013 11:16:17 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015