የፖለቲካ ካንሰራችንን ተጋግዘን ከማዳን - TopicsExpress



          

የፖለቲካ ካንሰራችንን ተጋግዘን ከማዳን በሽሙጥና ... እስከመቼ??? #Ethiopia #udj #eprdf ምንሊክ ሳልሳዊ :-በሃገሪቱ የተከሰተውን ደዌ ከማዳመጥ ይልቅ በሽሙጥ አንዱ አንዱን እየወገረው በመብረር ላይ እንገኛለን :;እርስ በእርስ ከመወጋገር ያድነን እንዳንል እየተወጋገርን ጸሎት ለቅጽበት ነው::ማን ከማን ይማር ሎሌ ከንጉሱ ሆኖብን ሆነና የራሳችንንም ሆነ የሃገራችንን ህመም ተጋግዘን እንዳናድን ራሳችን በሽታ ሆነናል::ምን እንደተባልን እንኳን ማዳመጥ አለመቻላችን አንዱ ደንቃራችን ሲሆን የምንናገረውንም ከማንነገርው መራርጠን መተንፈስ እስኪያቅተን ድረስ እያቃተትን በሽታችንን እያባስን ብዙሃዊ ተላላፊ ህመም አድርገነዋል ከዚህ ይሰውረን እንዳንል ራሳችን አሁንም ደንቃራ ሆነናል:: የኢትዮጵያችን ችግር የኢትዮጵያ የሃገር ችግር ሳይሆን የህዝቦች የጋራ የሆነ እና ገዢዎች የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::ልዩነት እንዳለ ሆኖ በጋራ ሃገራዊ መርህ ላይ ያልተመሰረተ ፖለቲካ እንዴት ህዝባዊ መተሳሰብ ሊፈጥር እንደሚችል በሃገራችን የሚገኙ ፖለቲከኝኣ ነን የሚሉ አልተረዱትም ወይንም አውቀው እየተባሉ እያባሉን እያነካከሱን ነው:: በጋራ መተሳሰብ ላይ ያልተመሰረተው ፖለቲካችን እና በመጭበርበር የሚያጭበረብሩን ገዢዎቻችን ለነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ አደገኛ የሆነ የፖለቲካ በሽታ እያወረኡ ይገኛሉ የፖለቲካ በሽታ ብቻ ሳይሆን በአንድ ወጥ መርህ ላይ የተመሰረተ እና የደቀቀ ኢኮኖሚ ጭምር:: ይህ በተጭበረበር ፖለቲካ ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ የህዝቦችን የጋራ መደጋገፍ ቢተይቅም ገዢው መደብ በፍጹም ከኔ ውጪ የሚነካ ካለ እሳት እንደነካ ነው በማለት በፍራቻ ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ዜጎች በሃገራቸው ብሄራዊ አጀንዳ ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዳይተሳሰቡ እንዳይደጋገፉ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል::ከማህበረሰቡ ተገልሎ እየተሰራ ያለውን ውጤት እያየነው ነው:: የገዢው ፓርቲ አይን እንዲገለጽልን ሱባዬ እየገባን ልናሳስበው የምንወደው ነገር ቢኖር ሃገር በምታድግበት ጊዜ መቀመቅ እየከተታት እንደሚገኝ ነው:: በሃገራችን በመጀመሪያ ደረጃ ሁሌ ለገዢዎቹ የሚኒነግራቸው ቢኖር የህግ የበላይነት እንዲከበር ነው:: የስልጥኣን እድሜ ለማስረዘም ሲባል በሃገሪቱ ገንዘብ የተገዙ የፓርቲ ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከህግ በላይ በመሆን አሳር እና አበሳ እያሳዩን ሲሆን ይህንንም ከተራ ዜጋ ጀምሮ እስከ ሃይማኖት መሪዎች ድረስ አበቱታ እያሰሙ የህግ ያለህ የመንግስት ያለህ እያሉ ነው::ሲታይ ግን ምንም መፍትሄ ያለው አይመስልም ይህ ደግሞ መንግስት ነኝ የሚለው አካል የስርኣት ለውጥ ማምታት እንዳለበት ሲያመለክት ለውጡን ተከትሎ ህግና ደንብ ሊከበር እንደሚችል የሚታወቅ እና የተጠና ነው::በዚሁ ከቀጠለ ግን አገር ከገባችበት አደጋ ወደ ሌአል አደገኛ አደጋ እንደምትሸጋገር ልመናገር እወዳለሁ:: ሌላው የተንሰራፋው ሙስና የሃገር ሃብትን በተገቢው ቦታ ላይ እንዳናውል እንቅፋት ሆኗል:: ሁልኡም በተደጋጋሚ የምንነገረው ታግለው ስልታን እንደያዙ የሚደነፉት የወያኔ ጁንታ አባላት በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው አገሪቷን እርቃኗን አስቀርተዋታል:: ይህ አደገኛ የሙስና ሂደት ህዝብን ወደ ኑር ውድነት እና ድህነት እስር ውስጥ ከቶታል:: ደጋግመን እንናገራለን እጅግ ሊለወጥ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ለማሳወቅ እንፈልጋልን::በተጨማሪ በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል:: የፖለቲካ ካንሰራችንን ተነጋግረን እና በጋራ ሆነን ከማዳን በጉልበት በሽሙጥ እና እኔ አውቅልሃለሁ በሚል አባዜ እስከመቼ ድረስ እንደምንቀጥል አልታወቀም::ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግመን ልንነገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው::ሁላችንም ዜጋ እስከሆንን ድረስ ለሃገራችን እኩል አስታውጾ ማበርከት አለብን እየተገፋን እስከመቼ???
Posted on: Fri, 18 Oct 2013 17:12:09 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015