ድምጻችን ይሰማ፡በደሴ እየተደበደብንም - TopicsExpress



          

ድምጻችን ይሰማ፡በደሴ እየተደበደብንም ትግላችን ይቀጥላል! እስርና ግርፋትን ሸሽተን መስጂዶቻችንን ባዶ አናደርጋቸውም! ከስድስት ወር በላይ መስጂዶቻችንን ተነጥቀን በየሜዳውና በየጎዳናው ስንሰግድ ነበረ ሲሆን ከዚህ በላይ ግን በየጎዳናው ላይ መስገድ አንችልም! ታላላቅና ያማሩ መስጂዶቻችን ከጎናችን ሁኖ ሳለ እኛ ግን መስጂዶቻችንን ባዶ አድርገን ሜዳ ላይ ወድቀን እንገኛለን፡፡ ከዚህ በፊት ከምንሳሳላቸው መስጂዶቻችን ላለመለየት ስንል ብዙ መስዋእትነቶችን መክፈላችን አይዘነጋም፡፡ፊታችን በመስተዋት ስባሪ እስከሚቀደድ ድረስ እንኳን መስዋእትነት ከፍለናል፡፡ የጭቆናው ቀንበር የበረታብን ጊዜ መስጂዶቻችንን ጥለን ጎዳና ላይ ወድቀናል፡፡ ያች ቀን ግን እንደ እሾህ እየወጋችን ቀንና ማታ እያሰቃየችን ትገኛለች፡፡ እየተደበደብንም ትግላችን ይቀጥላል የምንለው ጁምዓ ለምናሰማው ተቃውሞ ብቻ ሳይሆን መስጂዶቻችንን ለማስመለስ በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ነው፡፡ ከነገ ጀምረን የሚደርሱብንን እስርና ግርፋት እንዲሁም ስቃይ ተቋቁመን ሁላችንም ወደ መስጂዶቻችን በመመለስ ሁለተኛ ጀመዓ እንሰግዳለን! ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም! አላሁ አክበር!
Posted on: Mon, 08 Jul 2013 19:08:53 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015