ድምፃችን ይሰማ ማክሰኞ ሐምሌ - TopicsExpress



          

ድምፃችን ይሰማ ማክሰኞ ሐምሌ 16/2005 ጋዜጣዊ መግለጫ ፡ የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነትኮሚሽን ኢትዮጵያ የከሰሰቻቸውን የሃይማኖት ነጻነት ተሟጋቾች እንድትለቅ ጠየቀ ዋሺንግተን ዲሲ፡- ለሃይማኖታዊ ነጻነታቸው መከበር በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ሲያደርጉ የነበሩ ሙስሊሞች ላይ ፖሊስ ጥቃት የሰነዘረበት ክስተት አንድ አመት በተቆጠረበት በዚህ ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን /U.S. Commission on International Religious Freedom )USCIRF(/ የኢትዮጵያ መንግስት በወቅቱ አስሮ ለችሎት ያቀረባቸውን 29 ግለሰቦች እንዲፈታ ይጠይቃል፡፡ በሐምሌ 2004 መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አመራሮች ቦታ ነጻ ምርጫ እንዲደረግ በሰላማዊ መንገድ ሲጠይቁ የነበሩ በመቶዎችየሚቆጠሩ ሙስሊም ሰልፈኞችን አስሯል፡፡ በወቅቱ ከታሰሩት ውስጥ ብዙዎቹ ቢለቀቁም 29 ያህሉ ግን በጥር 2005 በመንግስት ጸረ ሽብርአዋጅ ‹‹ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም ርእዮተአለማዊ›› አላማን በሐይል ለማሳካት እና የሽብር ተግባርን ለመፈጸም በማሴር፣ በማቀድና በማዘጋጀት›› በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ሕግ ከሃይማኖት ነጻነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለውም በዚህ ወቅት ነበር፡፡ ‹‹የአትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ የሃይማኖት ነጻነት ጠያቂዎችን በማሰርና በፈጠራ የሽብር ውንጀላ በዝግ ችሎት በመክሰስ ቅዋሚያቸውን ለማፈን መጣሩ እጅግ በጣም ያሳስበናል፡፡ ችሎቱ አሁን ሊቆምና)እስረኞቹ( አሁኑኑ ሊለቀቁ ይገባል›› ይላሉ የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ሐላፊ ካትሪና ላንቶስ ስዌት፡፡ ‹‹የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን በታህሳስ 2004 ወደ ኢትዮጵያ በተጓዘበት ወቅት ከሃያ ዘጠኙ እስረኞች ጠበቆች ጋር ተገናኝተን፤ ደንበኞቻቸው ቶርች እንደተደረጉናበአሰቃቂ የእስር አያያዝ እንዳለፉ ሪፖርት አድርገውልናል፡፡ ከዚያ ወቅት በኋላም ኮሚሽኑ በየካቲት 2005 የተላለፈው ‹‹ጂሃዳዊ ሀረካት›› የተሰኘው ፕሮግራም እንደሚያሳስበው ገልጿል፡፡ ይህ መንግስት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያስተላለፈው ፕሮግራም ሰላማዊ ሰልፈኞቹንና ታሳሪዎቹን አሸባሪ አድርጎ በማቅረቡ የችሎቱን ውሳኔ ያዛባል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የተከሳሾች ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ነጻነት እና ሂደቱ መከበሩን ለማረጋገጥ ሲባል የሚያደርገውን የማሳመን ጥረት ማጎልበት አለበት፡፡›› መንግስትና መጅሊሱ መጤ የእስልምና አስተሳሰብ በሀይል በህብረተሰቡ ላይ ለመጫን የሚያደርጉትን ጥረት በመቃወም ከታህሳስ 2004 ጀምሮ ሙስሊሞች በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ ከጁምአ ስግደት በኋላ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ የተቃውሞ ሰልፎቹ ለስድስት ወራት ያህል ሲካሄዱ ባለሥልጣናቱ ያላስቆሙት ቢሆንም የተሳታፊዎቹ ቁጥር እያየለ ሲመጣ ሰልፈኞቹ ተቃውሞአቸውን እንዲገቱት ለማድረግ የጸጥታ ኃይሎች ሰልፈኞቹንና ቤተሰቦቻቸውን ማዋከብ መጀመራቸውን ሪፖርት አድርገዋል፡፡ የመጀመሪያው እስር የተካሄደው በሐምሌ 5 2004 ሌሊት ግለሰቦች ለምጽዋት እና ለተቃውሞ ፕሮግራም ከአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ጋር በተገጣጠመበት ወቅት በመስጂዱ ተሰባስበው እንዳለ ፖለስ መስጂዱን በኃይል ጥሶ በገባበት ወቅት ነው፡፡ ተቃዋሚዎች በፖሊስ መደብደባቸውና መታሰራቸው የተዘገበ ሲሆን ጥቂት እማኞችም ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ እና ቀጥታ ጥይት መጠቀሙን መስክረዋል፡፡ ፖሊስ የእስርተግባሩን በማጠናከር ሐምሌ 12 እና 13 / 2004 ጋዜጠኞችን ጨምሮሰላማዊ ሰልፈኞች ከመንግስት ጋር እንዲደራደሩ የመረጧቸው 17 የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የእስር ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሐምሌ 14/ 2004 ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ጥሶ በመግባት በርካቶችን አስሯል፡፡ እንደጊዜው እማኞች ምስክርነት ተቃወሚዎቹ የድብደባ፣ የአስለቃሽ ጢስ እና የእስር ሰለባ ሆነዋል፡፡ ከተከሳሾቹ ውስጥ ዘጠኝ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው አባላት፣ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት ዋና አዘጋጅ ዩሱፍ ጌታቸውና የቀድሞ የሲቪልሰርቪስ ሚኒስትሩ ጁነይዲ ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሐቢባ ሙሀመድ ይገኙበታል፡፡
Posted on: Tue, 23 Jul 2013 08:48:24 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015