ጁዝ 11፦ ከሱረቱ አት-ተውባህ 93 እስከ - TopicsExpress



          

ጁዝ 11፦ ከሱረቱ አት-ተውባህ 93 እስከ ሱረቱ ሁድ 5 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። 9:93 (የወቀሳ) መንገዱ በነዚያ እነሱ ባለጸጋዎች ሆነዉ ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ ሰዎች ላይ ብቻ ነዉ፣ ከቀሪዎቹ ጋር መኾናቸውን ወደዱ፤ አላህም በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው፣ ስለዚህ እነሱ አያውቁም። The cause [for blame] is only upon those who ask permission of you while they are rich. They are satisfied to be with those who stay behind, and Allah has sealed over their hearts, so they do not know. 9:94 ወደነሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ምክንያታቸውን ያቀርቡላችኋል፣ አታመካኙ፤ እናንተን ፈጽሞ አናምንም፤ አላህ ከወሬዎቻችሁ በእርግጥ ነግሮናልናአላህም ሥራችሁን በእርግጥ ያያል፤ መልክተኛውም (እንደዚሁ)፤ ከዚያም ሩቅንና ቅርብን ሁሉ ዐዋቂ ወደ ሆነው (አላህ) ትመለሳላችሁ ወዲያዉም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል በላቸው። They will make excuses to you when you have returned to them. Say, Make no excuse - never will we believe you. Allah has already informed us of your news. And Allah will observe your deeds, and [so will] His Messenger; then you will be taken back to the Knower of the unseen and the witnessed, and He will inform you of what you used to do. 9:95 ወደነሱ በተመለሳችሁ ጊዜ እንድትተውዋቸው ለናንተ በእርግጥ በአላህ ይምላሉ፤ እነሱንም ተውዋቸው፤ እነሱ እርኩሶች ናቸዉና፤ ይሠሩትም በነበሩት ዋጋ መኖሪያቸዉ ገሀነም ነው። They will swear by Allah to you when you return to them that you would leave them alone. So leave them alone; indeed they are evil; and their refuge is Hell as recompense for what they had been earning. 9:96 ከነሱ ትወዱላቸው ዘንድ ለናንተ ይምሉላችኋል፤ ከነሱ ብትወዱም አላህ ከአመጠኞች ሕዝቦች አይወድም። They swear to you so that you might be satisfied with them. But if you should be satisfied with them - indeed, Allah is not satisfied with a defiantly disobedient people. 9:97 አዕራቦች በክሕደትና በንፍቅና በጣም የበረቱ፤ አላህም በመልክተኛው ላይ ያወረደውን ሕግጋት ባለማወቅ የተገቡ ናቸው፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው። The bedouins are stronger in disbelief and hypocrisy and more likely not to know the limits of what [laws] Allah has revealed to His Messenger. And Allah is Knowing and Wise. 9:98 ከአዕራቦችም (በአላህ መንገድ) የሚያወጣዉን (ገንዘብ) ዕዳ አድርጎ የሚይዝ፣ በናንተም ላይ የጊዜን መገለባበጥ የሚጠባበቅ ሰው አልለ፤ በነሱ ላይ ጥፋቱ ይዙርባቸው፤ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው። And among the bedouins are some who consider what they spend as a loss and await for you turns of misfortune. Upon them will be a misfortune of evil. And Allah is Hearing and Knowing. 9:99 ከአዕራቦችም፣ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውንም (ምጽዋቶች) አላህ ዘንድ መቃረቢያዎችና ወደ መልክተኛው ጸሎቶችን መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ሰዉ አልለ፤ ንቁ፤ እርሷ ለነሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት፤ አላህ በችሮታው ውስጥ (በገነቱ) በእርግጥ ያስገባቸዋል፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና። But among the bedouins are some who believe in Allah and the Last Day and consider what they spend as means of nearness to Allah and of [obtaining] invocations of the Messenger. Unquestionably, it is a means of nearness for them. Allah will admit them to His mercy. Indeed, Allah is Forgiving and Merciful. 9:100 ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች፣ እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸዉ አላህ ከነሱ ወዷል፤ (*) ከርሱም ወደዋል፤ (**) በሥሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች፣ በዉስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲሆኑ ለነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፣ ይህ ታላቅ ዕድል ነው። * ሥራቸውን ተቀብሏል ** በተሠጣቸው ምንዳ ተደስተዋል And the first forerunners [in the faith] among the Muhajireen and the Ansar and those who followed them with good conduct - Allah is pleased with them and they are pleased with Him, and He has prepared for them gardens beneath which rivers flow, wherein they will abide forever. That is the great attainment. 9:101 በዙሪያችሁም ካሉት ከዐረብ ዘላኖች መናፍቃን አልሉ፤ ከመዲና ሰዎችም በንፍቅና ላይ በማመጽ የዘውተሩ አልሉ፤ አታዉቃቸውም፤ እኛ እናዉቃቸዋለን፤ ሁለት ጊዜ (*) እንቀጣቸዋለን ከዚያም ወደ ታላቅ ቅጣት ይመለሳሉ። * በወቅሳና በመቃብር ስቃይ And among those around you of the bedouins are hypocrites, and [also] from the people of Madinah. They have become accustomed to hypocrisy. You, [O Muhammad], do not know them, [but] We know them. We will punish them twice [in this world]; then they will be returned to a great punishment. 9:102 ሌሎቸም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ፤ (፬) መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አልሉ፤ አላህ ከነሱ ጸጸታቸውን ሊቀበል ይከጅላል፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነዉና። And [there are] others who have acknowledged their sins. They had mixed a righteous deed with another that was bad. Perhaps Allah will turn to them in forgiveness. Indeed, Allah is Forgiving and Merciful. 9:103 ከገንዘቦቻቸው ስትሆን በርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የሆነችን፣ ምጽዋት ያዝ፤ ለነሱም ጸልይላቸዉ፤ ጸሎትህ ለነሱ እርካታ ነዉና አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው። Take, [O, Muhammad], from their wealth a charity by which you purify them and cause them increase, and invoke [ Allah s blessings] upon them. Indeed, your invocations are reassurance for them. And Allah is Hearing and Knowing. 9:104 አላህ እርሱ ከባሮቹ ንስሐን የሚቀበል፣ ምጽዋቶችንም የሚወስድ መሆኑን አላህም እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ መሆኑን አያዉቁምን? Do they not know that it is Allah who accepts repentance from His servants and receives charities and that it is Allah who is the Accepting of repentance, the Merciful? 9:105 በላቸዉም፦ ሥሩ፤ አላህ ሥራችሁን በእርግጥ ያያልና መልክተኛውና ምእምናንም፤ (እንደዚሁ ያያሉ)። ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ ዐዋቂ ወደ ሆነዉም (አላህ) በእርግጥ ትመለሳላችሁ፤ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል። And say, Do [as you will], for Allah will see your deeds, and [so, will] His Messenger and the believers. And you will be returned to the Knower of the unseen and the witnessed, and He will inform you of what you used to do. 9:106 ሌሎችም ለአላህ ትእዛዝ የተቆዩ ሕዝቦች አልሉ ወይ ይቀጣቸዋል፤ ወይም ከነሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው። And [there are] others deferred until the command of Allah - whether He will punish them or whether He will forgive them. And Allah is Knowing and Wise. 9:107 እነዚያም (ምእምናንን) ለመጉዳት፣ ክሕደትንም ለማበርታት፣ በምእምናንም መካከል ለመለያየት ከአሁን በፊት አላህንና መልክተኛዉን የተዋጋዉንም ሰው ለመጠባበቅ መስጊድን የሠሩት (ከነሱ ናቸው)፤ መልካምን ሥራ እንጂ ሌላ አልሻንም ሲሉም በእርግጥ ይምላሉ፤ አላህም እነሱ በእርግጥ ዉሸታሞች መሆናቸዉን ይመሰክራል። And [there are] those [hypocrites] who took for themselves a mosque for causing harm and disbelief and division among the believers and as a station for whoever had warred against Allah and His Messenger before. And they will surely swear, We intended only the best. And Allah testifies that indeed they are liars. 9:108 በርሱ ዉስጥ በፍጹም አትስገድ፤ ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው (የቁባ) መስጊድ በዉስጡ ልትሰግድበት ይልቅ የተገባው ነው በሱ ዉስጥ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አልሉ፤ አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል። Do not stand [for prayer] within it - ever. A mosque founded on righteousness from the first day is more worthy for you to stand in. Within it are men who love to purify themselves; and Allah loves those who purify themselves. 9:109 አላህን በመፍራትና ዉዴታዉን በመፈለግ ላይ ግንቡን የመሠረተው ሰው ይበልጣን ወይስ ጎርፍ በሸረሸረው ለመናድ በተቃረበ ገደል አፋፍ ላይ ግንቡን የመሠረተውና በርሱ (ይዞት) በገሃነም እሳት ዉስጥ የወደቀ (ይበልጣል?) አላህም በደለኞች ሕዘቦችን አይመራም። Then is one who laid the foundation of his building on righteousness [with fear] from Allah and [seeking] His approval better or one who laid the foundation of his building on the edge of a bank about to collapse, so it collapsed with him into the fire of Hell? And Allah does not guide the wrongdoing people. 9:110 ያ የካቡት ግንባቸው ልቦቻቸው (በሞት) ካልተቆራረጡ በቀር፣ በልቦቻቸው ዉስጥ የመጠራጠር ምክንያት ከመሆን አይወገድም፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው። Their building which they built will not cease to be a [cause of] skepticism in their hearts until their hearts are stopped. And Allah is Knowing and Wise. 9:111 አላህ ከምእምናን፣ ነፍሶቻቸዉንና ገንዘቦቻቸዉን፣ ገነት ለነሱ ብቻ ያላቸው በመሆን ገዛቸው፤ በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ፤ ይገድላሉም፤ ይገደላሉም፤ በተዉራት፣ በኢንጅልና በቁርአንም፣ (የተነገረውን) ተስፋ በርሱ ላይ አረጋገጠ፤ ከአላህም የበለጠ በኪዳኑ የሚሞላ ማነዉ? በዚያም በርሱ በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ፤ ይህም እርሱ ታላቅ ዕድል ነው። Indeed, Allah has purchased from the believers their lives and their properties [in exchange] for that they will have Paradise. They fight in the cause of Allah , so they kill and are killed. [It is] a true promise [binding] upon Him in the Torah and the Gospel and the Quran. And who is truer to his covenant than Allah ? So rejoice in your transaction which you have contracted. And it is that which is the great attainment. 9:112 (እነርሱ) ተጸጻቺዎች፣ ተገዢዎች፣ አመስጋኞች ጿሚዎች፣ አጎንባሾች፣ በግንባር ተደፊዎች፣ በበጎ ሥራ አዛዦች፣ ከክፉም ከልካዮች የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው፤ ምእምናንንም አብስር። [Such believers are] the repentant, the worshippers, the praisers [of Allah ], the travelers [for His cause], those who bow and prostrate [in prayer], those who enjoin what is right and forbid what is wrong, and those who observe the limits [set by] Allah . And give good tidings to the believers. 9:113 ለነቢዩና ለነዚያ ላመኑት፣ ለአጋሪዎቹ የዝምድና፣ ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ፣ እነሱ (ከሐዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ምሕረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም። It is not for the Prophet and those who have believed to ask forgiveness for the polytheists, even if they were relatives, after it has become clear to them that they are companions of Hellfire. 9:114 የኢብራሂም ለአባቱ ምሕረትን መለመን፣ ለርሱ ገብቶለት ለነበረችዉ ቃል (ለመምላት) እንጂ ለሌላ አልነበረም። እርሱም የአላህ ጠላት መሆኑ ለርሱ በተገለጸለት ጊዜ፣ ከርሱ ራቀ፤ (ተወዉ)፤ ኢብራሂም በእርግጥ በጣም ርኅሩህ ታጋሽ ነውና። And the request of forgiveness of Abraham for his father was only because of a promise he had made to him. But when it became apparent to Abraham that his father was an enemy to Allah , he disassociated himself from him. Indeed was Abraham compassionate and patient. 9:115 አላህም ሕዝቦችን ከአቀናቸው በኋላ፣ የሚጠነቀቁትን (ሥራ) ለርሱ እስከሚገልጽላቸዉ፣ (እስከሚተዉትም) ድረስ ጥፋተኛ የሚያደርግ አይደለም፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነውና። And Allah would not let a people stray after He has guided them until He makes clear to them what they should avoid. Indeed, Allah is Knowing of all things. 9:116 አላህ የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፤ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፤ ለናንተም ከርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም። Indeed, to Allah belongs the dominion of the heavens and the earth; He gives life and causes death. And you have not besides Allah any protector or any helper. 9:117 በነቢዩ በነዚያም በችግሪቱ ጊዜያት (በተቡክ ዘመቻ) ከነሱ የከፊሎች ልቦች (ለመቅረት) ሊዘነበሉ ከተቃረቡ በኋላ፣ በተከተሉት ስደተኞችና ረዳቶች ላይ፣ አላህ በእርግጥ ጸጸታቸዉን ተቀበለ፤ ከዚያም ከነሱ ንስሐ መግባታቸውን ተቀበለ፤ እርሱ ለነሱ ርኅሩህ አዛኝ ነውና። Allah has already forgiven the Prophet and the Muhajireen and the Ansar who followed him in the hour of difficulty after the hearts of a party of them had almost inclined [to doubt], and then He forgave them. Indeed, He was to them Kind and Merciful. 9:118 በነዚያም በሦስቱ ሰዎች ላይ ምድር ከስፋትዋ ጋር በነሱ ላይ እስከ ጠበበች፣ ነፍሶቻቸውም በርሳቸዉ ላይ እስከ ተጠበቡ፣ ከአላህም ወደርሱ ቢሆን እንጂ ሌላ መጠጊያ አለመኖሩን እስከ አረጋገጡ ድረስ በተቆዩት ላይ፣ (አላህ ጸጸትን ተቀበለ)። ከዚያም ይጸጸቱ ዘንድ ወደ ጸጸት መራቸው፤ አላህ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነዉና። And [He also forgave] the three who were left behind [and regretted their error] to the point that the earth closed in on them in spite of its vastness and their souls confined them and they were certain that there is no refuge from Allah except in Him. Then He turned to them so they could repent. Indeed, Allah is the Accepting of repentance, the Merciful. 9:119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከዉነተኞቹም ጋር ሁኑ። O you who have believed, fear Allah and be with those who are true. 9:120 ለመዲና ሰዎችና ከአዕራብም በዙሪያቸው ላሉት ሰዎች፣ ከአላህ መልክተኛ ወደኋላ ሊቀሩ፣ ነፍሶቻቸውንም ከነፍሱ አብልጠው ሊወዱ አይገባቸውም ነበር፤ ይህ (ከመቅረት መከልከል) ለነርሱ መልካም ሥራ የሚጻፍላቸዉ ቢሆን እንጅ፣ በአላህ መንገድ ላይ ጥምም ድካምም፣ ረኃብም፣ የማይነካቸው፣ ከሐዲዎችንም የሚያስቆጭን ሰፍራ የማይረግጡ ከጠላትም የሚጎዳን ነገር (መግደልን መማረክን መዝረፍን) የማያገኙ፣ በመሆናቸው ነው። አላህ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና። It was not [proper] for the people of Madinah and those surrounding them of the bedouins that they remain behind after [the departure of] the Messenger of Allah or that they prefer themselves over his self. That is because they are not afflicted by thirst or fatigue or hunger in the cause of Allah , nor do they tread on any ground that enrages the disbelievers, nor do they inflict upon an enemy any infliction but that is registered for them as a righteous deed. Indeed, Allah does not allow to be lost the reward of the doers of good. 9:121 ትንሽንም ትልቅንም ልግስና አይለግሱም፣ ወንዝንም አያቋርጡም፣ አላህ ይሠሩት ከነበረው የበለጠን ምንዳ ይመነዳቸው ዘንድ ለነሱ የሚጻፍላቸው ቢሆን እንጂ። Nor do they spend an expenditure, small or large, or cross a valley but that it is registered for them that Allah may reward them for the best of what they were doing. 9:122 ምእምናንም (ነቢዩ ጋር ካልሆነ) በሙሉ ሊወጡ አይገባም፤ ከነሱ ዉስጥ ከየክፍሉ አንዲት ጭፍራ ለምን አትወጣም፤ (ሌሎቹ) ሃይማኖትን እንዲማሩና ወገኖቻቸውን ወደነርሱ በተመለሱ ጊዜ እንዲጠነቀቁ ይገሥጹዋቸው ዘንድ (ለምን አይቀሩም)። And it is not for the believers to go forth [to battle] all at once. For there should separate from every division of them a group [remaining] to obtain understanding in the religion and warn their people when they return to them that they might be cautious. 9:123 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአቅራቢያችሁ ያሉትን ከሐዲዎች ተዋጉ፤ ከናንተም ብርታትን ያግኙ፤ አላህም ከሚጠነቀቁት ጋር መሆኑን ዕወቁ። O you who have believed, fight those adjacent to you of the disbelievers and let them find in you harshness. And know that Allah is with the righteous. 9:124 ሱራም (ምዕራፍ) በተወረደች ጊዜ፣ ከነሱ (ከመናፍቃን) ዉስጥ ማንኛችሁ ነው? ይህቺ (ምዕራፍ) እምነትን የጨመረችለት የሚል ሰው አልለ፤ እነዚያ ያመኑትማ፣ የሚደሰቱ ሲሆኑ እምነትን ጨመረችላቸው። And whenever a surah is revealed, there are among the hypocrites those who say, Which of you has this increased faith? As for those who believed, it has increased them in faith, while they are rejoicing. 9:125 እነዚያም በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸውማ፣ በርክሰታቸዉ ላይ ርክሰትን ጨመረችላቸው፤ እነሱም ከሐዲዎች ሆነው ሞቱ። But as for those in whose hearts is disease, it has [only] increased them in evil [in addition] to their evil. And they will have died while they are disbelievers. 9:126 በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መሆናቸውን አያዩምን ? ከዚያም አይጸጸቱምን? እነሱም አይገሠጹምን? Do they not see that they are tried every year once or twice but then they do not repent nor do they remember? 9:127 (እነሱን የምታነሳ) ምዕራፍም) በተወረደች ጊዜ አንድ ሰው ያያችኋልን? እያሉ፣ ከፊሎቻቸው ወደ ከፊሉ ይመለከታሉ፤ ከዚያም (ተደበቀው) ይኼዳሉ፤ እነርሱ የማያዉቁ ሕዝቦች በመሆናቸው አላህ ልቦቻቸውን አዞረ። And whenever a surah is revealed, they look at each other, [saying], Does anyone see you? and then they dismiss themselves. Allah has dismissed their hearts because they are a people who do not understand. 9:128 ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በርሱ ላይ ጥኑ የሆነ፣ በናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ርኅሩህ አዛኝ የሆነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ። There has certainly come to you a Messenger from among yourselves. Grievous to him is what you suffer; [he is] concerned over you and to the believers is kind and merciful. 9:129 ቢያፈገፍጉም አላህ በቂዬ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ በርሱ ላይ ተጠጋሁ፤ እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው በላቸው። But if they turn away, [O Muhammad], say, Sufficient for me is Allah ; there is no deity except Him. On Him I have relied, and He is the Lord of the Great Throne. 10:1 አ.ላ.ራ. (አሊፍ፣ ላም፣ ራ፤)(1) እነዚህ፥ በጥበብ የተሞላው መጽሐፍ አንቀጾች ናቸው። (1) እኔ አላህ ነኝ አያለሁ። Alif, Lam, Ra. These are the verses of the wise Book 10:2 ሰዎችን አስፈራራ፤ እነዚያንም ያመኑትን ለነሰ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን አብስር በማለት ከነሱ ወደ ኾነ ለሰዎች፣ ከነርሱ ለሆነ አንድ ሰው፦ የሰው ልጆችን አስጠንቅቅ፥ አማኞችንም ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ እንደሚጠብቃቸው አብስር። የሚል ራዕይ መግለጻችን አስደነቃቸውን? ከሐዲያን ይህ ግልጽ ደጋሚ ነው። አሉ። Have the people been amazed that We revealed [revelation] to a man from among them, [saying], Warn mankind and give good tidings to those who believe that they will have a [firm] precedence of honor with their Lord? [But] the disbelievers say, Indeed, this is an obvious magician. 10:3 ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፥ በዐርሹም ላይ ራሱን ያደላደለ (አምላክ)ነው። ነገሮችን (ሁሉ) ያስተናብራል፥ ይመራል። ከርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር (የሚያማልድ) አንድም አማላጅ የለም። ጌታችሁ አላህ ይህ ነው። ስለሆነም (በብቸኝነት) አምልኩት።አትገለፁምን?ር Indeed, your Lord is Allah , who created the heavens and the earth in six days and then established Himself above the Throne, arranging the matter [of His creation]. There is no intercessor except after His permission. That is Allah , your Lord, so worship Him. Then will you not remember? 10:4 (በኋላም)መመለሻቹሁ ወደርሱ ብቻ ነው። የአላህ ቃልኪዳን እውነትና የተረጋገጠ ነው። እርሱ የመፍጠረን ሂደት ይጀምራል። ከዚያም፤ ለእነዚያ ላመኑትና መልካም ሥራቸውን ለሠሩት ፍትሃዊ ምንዳን ሊለግስ፤ (ፍጡራኑም ከሞት)ይመልሳል። ግና እነዚያ የካዱት ወገኖች በክህደታቸው ሳቢያ የፍል ውሃ መጠጥ፤ አሳማሚ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል። To Him is your return all together. [It is] the promise of Allah [which is] truth. Indeed, He begins the [process of] creation and then repeats it that He may reward those who have believed and done righteous deeds, in justice. But those who disbelieved will have a drink of scalding water and a painful punishment for what they used to deny. 10:5 እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን (1)የለካ ነው፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ (በከንቱ) አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡ (1) በ28 ሌሊት ማደሪያዎችን It is He who made the sun a shining light and the moon a derived light and determined for it phases - that you may know the number of years and account [of time]. Allah has not created this except in truth. He details the signs for a people who know 10:6 ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህም በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ፡፡ Indeed, in the alternation of the night and the day and [in] what Allah has created in the heavens and the earth are signs for a people who fear Allah 10:7 እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩ ቅርቢቱንም ሕይወት የወደዱ በእሷም የረኩ እነዚያም እነሱ ከአንቀጾቻችን ዘንጊዎች የኾኑ፡፡ Indeed, those who do not expect the meeting with Us and are satisfied with the life of this world and feel secure therein and those who are heedless of Our signs 10:8 እነዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው፡፡ For those their refuge will be the Fire because of what they used to earn. 10:9 እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት (የገነትን መንገድ) ይመራቸዋል፡፡ ከሥራቸው ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ Indeed, those who have believed and done righteous deeds - their Lord will guide them because of their faith. Beneath them rivers will flow in the Gardens of Pleasure 10:10 በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት) ነው፡፡ በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይሁን (ማለት) ነው፡፡ Their call therein will be, Exalted are You, O Allah , and their greeting therein will be, Peace. And the last of their call will be, Praise to Allah , Lord of the worlds! 10:11 አላህ ለሰዎች ደግን ነገር ለማግኘት እንደ መቻኮላቸው (አጥፋን ሲሉት) ክፉን ነገር ቢያስቸኩል ኖሮ ጊዜያቸው ወደነሱ በተፈጸመ ነበር፡፡ እነዚያንም መገናኘታችንን የማይፈሩትን በጥመታቸው ውስጥ የሚዋልሉ ሲኾኑ እንተዋቸዋለን፡፡ And if Allah was to hasten for the people the evil [they invoke] as He hastens for them the good, their term would have been ended for them. But We leave the ones who do not expect the meeting with Us, in their transgression, wandering blindly 10:12 ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ በጎኑ ላይ ተጋድሞ ወይም ተቀምጦ ወይም ቆሞ ይለምነናል፡፡ ጉዳቱንም ከእሱ ላይ በገለጥንለት ጊዜ ወደ አገኘው ጉዳት እንዳልጠራን ሆኖ ያልፋል፡፡ እንደዚሁ ለድንበር አላፊዎች ይሠሩት የነበሩት ሥራ ተሸለመላቸው፡፡ And when affliction touches man, he calls upon Us, whether lying on his side or sitting or standing; but when We remove from him his affliction, he continues [in disobedience] as if he had never called upon Us to [remove] an affliction that touched him. Thus is made pleasing to the transgressors that which they have been doing 10:13 ከእናንተ በፊት የነበሩትንም የክፍለ ዘመናት ሰዎች መልክተኞቻቸው በማስረጃዎች የመጧቸው ሲኾኑ በበደሉና የማያምኑም በኾኑ ጊዜ በእርግጥ አጠፋናቸው፡፡ እንደዚሁ ተንኮለኞችን ሕዝቦች እንቀጣለን፡፡ And We had already destroyed generations before you when they wronged, and their messengers had come to them with clear proofs, but they were not to believe. Thus do We recompense the criminal people 10:14 ከዚያም እንዴት እንደምትሠሩ ልንመለከት ከእነሱ በኋላ በምድር ላይ ምትኮች አደረግናችሁ፡፡ Then We made you successors in the land after them so that We may observe how you will do. 10:15 አንቀጾቻችንም ግልጽ ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው ይላሉ፡፡ እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም፡፡ ወደእኔ የሚወርደውን እንጂ አልከተልም፡፡ እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ በላቸው፡፡ And when Our verses are recited to them as clear evidences, those who do not expect the meeting with Us say, Bring us a Quran other than this or change it. Say, [O Muhammad], It is not for me to change it on my own accord. I only follow what is revealed to me. Indeed I fear, if I should disobey my Lord, the punishment of a tremendous Day. 10:16 አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባለነበብኩትም (አላህ) እርሱን ባላሳወቃችሁም ነበር፡፡ በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት (ምንም ሳልል) ብዙን ዕድሜ(1) በእርግጥ ኖሬአለሁ፤ አታውቁምን (1) አርባ ዓመት Say, If Allah had willed, I would not have recited it to you, nor would He have made it known to you, for I had remained among you a lifetime before it. Then will you not reason? 10:17 በአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነሆ አመጸኞች አይድኑም፡፡ So who is more unjust than he who invents a lie about Allah or denies His signs? Indeed, the criminals will not succeed 10:18 ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡ And they worship other than Allah that which neither harms them nor benefits them, and they say, These are our intercessors with Allah Say, Do you inform Allah of something He does not know in the heavens or on the earth? Exalted is He and high above what they associate with Him 10:19 ሰዎችም አንድ ሕዝብ እንጂ ሌላ አልነበሩም፡፡ ተለያዩም፡፡ ከጌታህ ያለፈች ቃልም ባልነበረች ኖሮ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ (በቶሎ) በተፈረደ ነበር፡፡ And mankind was not but one community [united in religion], but [then] they differed. And if not for a word that preceded from your Lord, it would have been judged between them [immediately] concerning that over which they differ. 10:20 በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡ And they say, Why is a sign not sent down to him from his Lord? So say, The unseen is only for Allah [to administer], so wait; indeed, I am with you among those who wait. 10:21 ሰዎችንም ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን (ዝናብና ምቾትን) ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነሱ በተዓምራቶቻችን (በማላገጥ) ተንኮል ይኖራቸዋል፡፡ አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ መልክተኞቻችን(1) የምትመክሩትን ነገር በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው፡፡ (1) ተጠባባቂዎቹ መላዕክት። And when We give the people a taste of mercy after adversity has touched them, at once they conspire against Our verses. Say, Allah is swifter in strategy. Indeed, Our messengers record that which you conspire 10:22 እርሱ (አላህ) ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው፡፡ በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም(1) በመልካም ነፋስ በርሷ የተደሰቱ ኾነው (መርከቦቹ) በተንሻለሉ ጊዜ ኀይለኛ ነፋስ ትመጣባታለች፡፡ ከየስፍራውም ማዕበል ይመጣባቸዋል፡፡ እነሱም (ለጥፋት) የተከበቡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ (ያን ጊዜ) አላህን ከዚህች (ጭንቀት) ብታድነን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን ሲሉ ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይለምኑታል፡፡ (1) በተሣፋሪዎቹ It is He who enables you to travel on land and sea until, when you are in ships and they sail with them by a good wind and they rejoice therein, there comes a storm wind and the waves come upon them from everywhere and they assume that they are surrounded, supplicating Allah , sincere to Him in religion, If You should save us from this, we will surely be among the thankful. 10:23 በአዳናቸውም ጊዜ እነሱ ወዲያውኑ ያለ አግባብ በምድር ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ እናንተ ሰዎች ሆይ! ወሰን ማለፋችሁ (ጥፋቱ) በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው፡፡ (እርሱም) የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደኛ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እንነግራችኋለን፡፡ But when He saves them, at once they commit injustice upon the earth without right. O mankind, your injustice is only against yourselves, [being merely] the enjoyment of worldly life. Then to Us is your return, and We will inform you of what you used to do. 10:24 የቅርቢቱ ሕይወት ምሳሌ(1) ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ፣ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት (እንደ ፋፋ) ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋም በርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው፡፡ እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡ (1) ጊዜዋ በማጠርና በመጥፋት The example of [this] worldly life is but like rain which We have sent down from the sky that the plants of the earth absorb - [those] from which men and livestock eat - until, when the earth has taken on its adornment and is beautified and its people suppose that they have capability over it, there comes to it Our command by night or by day, and We make it as a harvest, as if it had not flourished yesterday. Thus do We explain in detail the signs for a people who give thought. 10:25 አላህም ወደ ሰላም አገር(1) ይጠራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡ (1) ወደ ገነት And Allah invites to the Home of Peace and guides whom He wills to a straight path 10:26 ለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገርና ጭማሪም አላቸው፡፡ ፊቶቻቸውንም ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸውም፡፡ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ For them who have done good is the best [reward] and extra. No darkness will cover their faces, nor humiliation. Those are companions of Paradise; they will abide therein eternally 10:27 ለእነዚያም ኃጢአቶችን ለሠሩት የኃጢኣቲቱ ቅጣት በብጤዋ አለቻቸው፡፡ ውርደትም ትሸፍናቸዋለች፡፡ ለእነሱ ከአላህ (ቅጣት) ጠባቂ የላቸውም፡፡ ፊቶቻቸው ከጨለመ ሌሊት ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይኾናሉ፡፡ እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው፡፡ But they who have earned [blame for] evil doings - the recompense of an evil deed is its equivalent, and humiliation will cover them. They will have from Allah no protector. It will be as if their faces are covered with pieces of the night - so dark [are they]. Those are the companions of the Fire; they will abide therein eternally. 10:28 ሁሉንም የምንሰበስባቸውን ከዚያም ለእነዚያ ለአጋሩት እናንተም ተጋሪዎችሁም ስፍራችሁን ያዙ የምንልበትን ተጋሪዎቻቸውም(1) እኛን ትገዙ አልነበራችሁም የሚሉዋቸው ሲኾኑ በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ (1) ጣዖቶቻችሁ And [mention, O Muhammad], the Day We will gather them all together - then We will say to those who associated others with Allah , [Remain in] your place, you and your partners. Then We will separate them, and their partners will say, You did not used to worship us, 10:29 «(ጣዖታቶቹ ለእኛ) ከመገዛታችሁ በእርግጥ ዘንጊዎች ለመኾናችንም በእኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ» (ይሏቸዋል)፡፡ And sufficient is Allah as a witness between us and you that we were of your worship unaware. 10:30 በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች፡፡ (አጋሪዎች) ወደ አላህም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ፡፡ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ይጠፋቸዋል፡፡ There, [on that Day], every soul will be put to trial for what it did previously, and they will be returned to Allah , their master, the Truth, and lost from them is whatever they used to invent. 10:31 «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡ Say, Who provides for you from the heaven and the earth? Or who controls hearing and sight and who brings the living out of the dead and brings the dead out of the living and who arranges [every] matter? They will say, Allah , so say, Then will you not fear Him? 10:32 እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ (ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ For that is Allah , your Lord, the Truth. And what can be beyond truth except error? So how are you averted? 10:33 እንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ላይ እነርሱ የማያምኑ መሆናቸው ተረጋገጠች፡፡ Thus the word of your Lord has come into effect upon those who defiantly disobeyed - that they will not believe. 10:34 «ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ውስጥ መፍጠርን የሚጀምር ከዚም የሚመልሰው አለን» በላቸው፡፡ «አላህ መፍጠርን ይጀምራል፤ (1)ከዚያም ይመልሰዋል፡፡ ታዲያ (ከእምነት) እንዴት ትዞራላችሁ» በላቸው፡፡ (1) ያልነበረን ያስገኛል። Say, Are there of your partners any who begins creation and then repeats it? Say, Allah begins creation and then repeats it, so how are you deluded? 10:35 «ከምታጋሩዋቸው፤(1) ወደ እውነት የሚመራ አለን» በላቸው፡፡ «አላህ ወደ እውነቱ ይመራል፡፡ ወደ እውነት የሚመራው ሊከተሉት የተገባው ነውን ወይስ ካልተመራ በስተቀር የማይመራው ለእናንተም ምን (አስረጅ) አላችሁ እንዴት (በውሸት) ትፈርዳላችሁ» በላቸው፡፡ (1) ለአላህ ባላጋራ ከምታደርጓቸው ጣዖታት Say, Are there of your partners any who guides to the truth? Say, Allah guides to the truth. So is He who guides to the truth more worthy to be followed or he who guides not unless he is guided? Then what is [wrong] with you - how do you judge? 10:36 አብዛኞቻቸውም ጥርጣሬን እንጂ አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬ ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ And most of them follow not except assumption. Indeed, assumption avails not against the truth at all. Indeed, Allah is Knowing of what they do. 10:37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው፡፡ And it was not [possible] for this Quran to be produced by other than Allah , but [it is] a confirmation of what was before it and a detailed explanation of the [former] Scripture, about which there is no doubt, from the Lord of the worlds. 10:38 በእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ፡፡ እውነተኞች እንደሆናችሁ (ተጋግዛችሁ አምጡ)» በላቸው፡፡ Or do they say [about the Prophet], He invented it? Say, Then bring forth a surah like it and call upon [for assistance] whomever you can besides Allah , if you should be truthful. 10:39 ይልቁንም (ከቁርኣን) እውቀቱን ባላደረሱት ፍቹም ገና ባልመጣቸው ነገር አስተባበሉ፡፡ እንደዚሁ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ የበዳዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት፡፡ Rather, they have denied that which they encompass not in knowledge and whose interpretation has not yet come to them. Thus did those before them deny. Then observe how was the end of the wrongdoers. 10:40 ከእነርሱም ውስጥ (ወደፊት) በርሱ የሚያምኑ አልሉ፡፡ ከእነርሱም በእርሱ የማያምኑ አልሉ፡፡ ጌታህም አጥፊዎቹን በጣም ዐዋቂ ነው፡፡ And of them are those who believe in it, and of them are those who do not believe in it. And your Lord is most knowing of the corrupters 10:41 «ቢያስተባብሉህም ለእኔ ሥራዬ አለኝ፡፡ ለእናንተም ሠራችሁ አላችሁ፡፡ እናንተ ከምሠራው ነገር ንጹሕ ናችሁ፡፡ እኔም ከምትሠሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ And if they deny you, [O Muhammad], then say, For me are my deeds, and for you are your deeds. You are disassociated from what I do, and I am disassociated from what you do. 10:42 ከእነሱም ወደ አንተ የሚያዳምጡ (እና የማያምኑ) አልሉ፡፡ አንተ ደንቆሮዎችን የማያውቁ ቢኾኑም ታሰማለህን And among them are those who listen to you. But can you cause the deaf to hear, although they will not use reason? 10:43 ከእነሱም ወደ አንተ የሚመለከቱ አልሉ፡፡ አንተ (ልበ) ዕውራንን የማያዩ ቢኾኑም ትመራለህን And among them are those who look at you. But can you guide the blind although they will not [attempt to] see? 10:44 አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡ Indeed, Allah does not wrong the people at all, but it is the people who are wronging themselves. 10:45 (ከሓዲዎችን) ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ እንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን (አስታውስ)፡፡ እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት በእርግጥ ከሰሩ የተመሩም አልነበሩም፡፡ And whether We show you some of what We promise them, [O Muhammad], or We take you in death, to Us is their return; then, [either way], Allah is a witness concerning what they are doing 10:46 የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡ ወይም (ሳናሳይህ) ብንገድልህ መመለሻቸው ወደ እኛ ነው፡፡ ከዚያም አላህ በሚሠሩት ስራ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡ And for every nation is a messenger. So when their messenger comes, it will be judged between them in justice, and they will not be wronged 10:47 ለሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛ አላቸው፡፡ መልክተኛውም በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉ) በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ And they say, When is [the fulfillment of] this promise, if you should be truthful? 10:48 «እውነተኞችም ከሆናችሁ ይህ (የቅጣቱ) ቀጠሮ መቼ ነው» ይላሉ፡፡ Say, I possess not for myself any harm or benefit except what Allah should will. For every nation is a [specified] term. When their time has come, then they will not remain behind an hour, nor will they precede [it]. 10:49 «ለራሴ ጉዳትንም ጥቅምንም አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም፡፡ ለሕዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አልላቸው፡፡ ጊዜያቸው በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም» በላቸው፡፡ Say, Have you considered: if His punishment should come to you by night or by day - for which [aspect] of it would the criminals be impatient? 10:50 «ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ፤ አጋሪዎቹ ከርሱ የሚቻኮሉበት ነገር ምንድን ነው ንገሩኝ» በላቸው፡፡ Then is it that when it has [actually] occurred you will believe in it? Now? And you were [once] for it impatient 10:51 «ከዚያም (ቅጣቱ) በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን በእርግጥ በእርሱ የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን» (ይባላሉ)፡፡ Then is it that when it has [actually] occurred you will believe in it? Now? And you were [once] for it impatient 10:52 ከዚያም ለእነዚያ ለበደሉት፡- «ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ትሠሩት የነበረችሁትን ዋጋ እንጂ አትመነዱም» ይባላሉ፡፡ Then it will be said to those who had wronged, Taste the punishment of eternity; are you being recompensed except for what you used to earn? 10:53 እርሱም(1) «እውነት ነውን» (ሲሉ) ይጠይቁሃል፡፡ «አዎን፤ በጌታዬ እምላለሁ፤ እርሱ እውነት ነው፡፡ እናንተም አምላጮች አይደላችሁም፤» በላቸው፡፡ (1) የምታስፈራራብን ነገር And they ask information of you, [O Muhammad], Is it true? Say, Yes, by my Lord. Indeed, it is truth; and you will not cause failure [to Allah ]. 10:54 ለበደለችም ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ቢኖራት ኖሮ በእርግጥ በተበዠችበት ነበር፡፡ ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጻሉ፡፡ በመካከላቸውም በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ And if each soul that wronged had everything on earth, it would offer it in ransom. And they will confide regret when they see the punishment; and they will be judged in justice, and they will not be wronged 10:55 ንቁ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ንቁ! የአላህ ተስፋ ቃል እርግጥ ነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ Unquestionably, to Allah belongs whatever is in the heavens and the earth. Unquestionably, the promise of Allah is truth, but most of them do not know 10:56 እርሱ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ He gives life and causes death, and to Him you will be returned 10:57 እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡ O mankind, there has to come to you instruction from your Lord and healing for what is in the breasts and guidance and mercy for the believers. 10:58 «በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡ Say, In the bounty of Allah and in His mercy - in that let them rejoice; it is better than what they accumulate. 10:59 «አላህ ከሲሳይ ለእናንተ ያወረደውን ከእርሱም እርምና የተፈቀደ ያደረጋችሁትን አያችሁን» በላቸው፡፡ «አላህ (ይህንን) ለእናንተ ፈቀደላችሁን ወይስ በአላህ ላይ ትቀጣጥፋላችሁ» በላቸው፡፡ Say, Have you seen what Allah has sent down to you of provision of which you have made [some] lawful and [some] unlawful? Say, Has Allah permitted you [to do so], or do you invent [something] about Allah ? 10:60 |የእነዚያም በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ (ሰዎች) በትንሣኤ ቀን (በአላህ) ጥርጣሬያቸው ምንድን ነው (አይቀጡም ይመስላቸዋልን) አላህ በሰዎች ላይ (ቅጣትን ባለማቻኮል) የልግስና ባለቤት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ አያመሰግኑም፡፡ And what will be the supposition of those who invent falsehood about Allah on the Day of Resurrection? Indeed, Allah is full of bounty to the people, but most of them are not grateful. 10:61 (ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛውም ነገር ላይ አትሆንም፣ ከርሱም ከቁርኣን አታነብም፣ ማንኛውንም ሥራ (አንተም ሰዎቹም) አትሠሩም በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ፡፡ በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል ከጌታህ (ዕውቀት) አይርቅም፡፡ ከዚያም ያነሰ የተለቀም የለም፤ በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ፡፡ And, [O Muhammad], you are not [engaged] in any matter or recite any of the Quran and you [people] do not do any deed except that We are witness over you when you are involved in it. And not absent from your Lord is any [part] of an atoms weight within the earth or within the heaven or [anything] smaller than that or greater but that it is in a clear register. 10:62 ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡ Unquestionably, [for] the allies of Allah there will be no fear concerning them, nor will they grieve 10:63 (እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው፡፡ Those who believed and were fearing Allah 10:64 ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ For them are good tidings in the worldly life and in the Hereafter. No change is there in the words of Allah . That is what is the great attainment. 10:65 ንግግራቸውም(1) አያሳዝንህ፡፡ ኀይል ሁሉ በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡ (1) መልዕክተኛ አይደለህም ማለታቸው And let not their speech grieve you. Indeed, honor [due to power] belongs to Allah entirely. He is the Hearing, the Knowing. 10:66 ንቁ! በሰማያት ያሉትና በምድርም ያሉት ሁሉ በእርግጥ የአላህ ናቸው፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ ተጋሪዎችን የሚጠሩ ምንን ይከተላሉ ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ አይደሉም፡፡ Unquestionably, to Allah belongs whoever is in the heavens and whoever is on the earth. And those who invoke other than Allah do not [actually] follow [His] partners. They follow not except assumption, and they are not but falsifying 10:67 እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ)፤ ቀንንም (ልትሠሩበት) ብርሃን ያደረገላችሁ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ፡፡ It is He who made for you the night to rest therein and the day, giving sight. Indeed in that are signs for a people who listen. 10:68 «አላህ ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ (ከሚሉት) ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ ተብቃቂ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ እናንተ ዘንድ በዚህ (በምትሉት) ምንም አስረጅ የላችሁም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን They have said, Allah has taken a son. Exalted is He; He is the [one] Free of need. To Him belongs whatever is in the heavens and whatever is in the earth. You have no authority for this [claim]. Do you say about Allah that which you do not know? 10:69 «እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ፈጽሞ አይድኑም፤» በላቸው፡፡ Say, Indeed, those who invent falsehood about Allah will not succeed. 10:70 (እነሱ) በቅርቢቱ ዓለም መጠቀም አላቸው፡፡ ከዚያም መመለሻቸው ወደእኛ ነው፡፡ ከዚያም ይክዱ በነበሩት ምክንያት ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን፡፡ [For them is brief] enjoyment in this world; then to Us is their return; then We will make them taste the severe punishment because they used to disbelieve 10:71 የኑሕንም ወሬ በእነሱ ላይ አንብብላቸው፡፡ ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙ ጊዜ መቆየቴ በአላህም ተዓምራት ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆን፤ በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ፡፡ ነገራችሁንም ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ጋር ሆናችሁ ቁረጡ፡፡ ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን (ግለጹት)፡፡ ከዚያም (የሻችሁትን) ወደእኔ አድርሱ፡፡ ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)፡፡» And recite to them the news of Noah, when he said to his people, O my people, if my residence and my reminding of the signs of Allah has become burdensome upon you - then I have relied upon Allah . So resolve upon your plan and [call upon] your associates. Then let not your plan be obscure to you. Then carry it out upon me and do not give me respite. 10:72 «ብትሸሹም (አትጎዱኝም)፡፡ ከምንዳ ምንንም አልለምናችሁምና፡፡ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ፡፡» And if you turn away [from my advice] then no payment have I asked of you. My reward is only from Allah , and I have been commanded to be of the Muslims. 10:73 አስተባበሉትም፡፡ እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትንም በታንኳይቱ ውስጥ አዳንናቸው፡፡ (ለጠፉት) ምትኮችም አደረግናቸው፡፡ እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን አሰጠምን፡፡ የተስፈራሩትም ሕዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ And they denied him, so We saved him and those with him in the ship and made them successors, and We drowned those who denied Our signs. Then see how was the end of those who were warned. 10:74 ከዚያም ከእርሱ በኋላ መልክተኞችን ወደየሕዝቦቻቸው ላክን፡፡ በግልጽ ማስረጃዎችም መጧቸው፡፡ (ከመላካቸው) በፊት በእርሱ ባስተባበሉበትም ነገር፤ የሚያምኑ አልሆኑም፡፡ እንደዚሁ በወሰን አላፊዎች ልቦች ላይ እናትማለን፡፡ Then We sent after him messengers to their peoples, and they came to them with clear proofs. But they were not to believe in that which they had denied before. Thus We seal over the hearts of the transgressors 10:75 ከዚያም ከእነሱ ኋላ ሙሳንና ሃሩንን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቱ በተዓምራታችን ላክን፡፡ ኮሩም ትዕቢተኞች ሕዝቦችም ነበሩ፡፡ Then We sent after them Moses and Aaron to Pharaoh and his establishment with Our signs, but they behaved arrogantly and were a criminal people 10:76 ከእኛም ዘንድ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ So when there came to them the truth from Us, they said, Indeed, this is obvious magic. 10:77 ሙሳ አለ፡- «እውነቱን በመጣላችሁ ጊዜ ድግምተኞች የማይድኑ ሲኾኑ (እርሱ ድግምት ነው) ትላላችሁን ይህ ድግምት ነውን» Moses said, Do you say [thus] about the truth when it has come to you? Is this magic? But magicians will not succeed. 10:78 (እነርሱም) አሉ፡- «አባቶቻችንን በእርሱ ላይ ካገኘንበት ሃይማኖት ልታዞረን ለእናንተም በምድር ውስጥ ኩራት (ሹመት) ልትኖራችሁ መጣህብን እኛም ለእናንተ አማኞች አይደለንም፡፡» They said, Have you come to us to turn us away from that upon which we found our fathers and so that you two may have grandeur in the land? And we are not believers in you. 10:79 ፈርዖንም፡- «ዐዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ» አለ፡፡ And Pharaoh said, Bring to me every learned magician. 10:80 ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ሙሳ ለእነርሱ፡- «እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ» አላቸው፡፡ So when the magicians came, Moses said to them, Throw down whatever you will throw. 10:81 (ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ያ በርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው፡፡ አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል፡፡ አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና፡፡» And when they had thrown, Moses said, What you have brought is [only] magic. Indeed, Allah will expose its worthlessness. Indeed, Allah does not amend the work of corrupters. 10:82 አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡ And Allah will establish the truth by His words, even if the criminals dislike it. 10:83 ለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን ከመፍራት ጋር ከወገኖቹ የኾኑ ጥቂቶች ትውልዶች እንጂ አላመኑለትም፡፡ ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ የኮራ ነበር፡፡ እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር፡፡ But no one believed Moses, except [some] youths among his people, for fear of Pharaoh and his establishment that they would persecute them. And indeed, Pharaoh was haughty within the land, and indeed, he was of the transgressors 10:83 ሙሳም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ ታዛዦች እንደ ሆናችሁ (በአላህ ላይ ትመካላችሁ)፡፡» And Moses said, O my people, if you have believed in Allah , then rely upon Him, if you should be Muslims. 10:85 አሉም፡- «በአላህ ላይ ተጠጋን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለበደለኞች ሕዝቦች መፈተኛ አታድርገን፡፡» So they said, Upon Allah do we rely. Our Lord, make us not [objects of] trial for the wrongdoing people 10:86 በእዝነትህም ከከሓዲዎች ሕዝቦች አድነን፡፡ And save us by Your mercy from the disbelieving people. 10:87 ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡- «ለሕዝቦቻችሁ በምስር ቤቶችን ሥሩ፡፡ ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ፡፡ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡ (ለሙሳ) ምእምናኖቹንም አብስር» ስንል ላክን፡፡ And We inspired to Moses and his brother, Settle your people in Egypt in houses and make your houses [facing the] qiblah and establish prayer and give good tidings to the believers. 10:88 ሙሳም አለ፡- «ጌታችን ሆይ! አንተ ለፈርዖንና ለሹሞቹ በቅርቢቱ ሕይወት ጌጥን ብዙ ገንዘቦችንም በእርግጥ ሰጠህ፡፡ ጌታችን ሆይ! ከመንገድህ ያሳስቱ ዘንድ (ሰጠሃቸው)፡፡ ጌታችን ሆይ! ገንዘቦቻቸውን አጥፋ፡፡ በልቦቻቸውም ላይ አትም፡፡ አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ አያምኑምና፡፡» And Moses said, Our Lord, indeed You have given Pharaoh and his establishment splendor and wealth in the worldly life, our Lord, that they may lead [men] astray from Your way. Our Lord, obliterate their wealth and harden their hearts so that they will not believe until they see the painful punishment. 10:89 (አላህም) «ጸሎታችሁ በእርግጥ ተሰምታለች፡፡ ቀጥም በሉ፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሰዎች መንገድ አትከተሉ» አላቸው፡፡ [ Allah ] said, Your supplication has been answered. So remain on a right course and follow not the way of those who do not know. 10:90 የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ፡፡ And We took the Children of Israel across the sea, and Pharaoh and his soldiers pursued them in tyranny and enmity until, when drowning overtook him, he said, I believe that there is no deity except that in whom the Children of Israel believe, and I am of the Muslims. 10:91 ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክ ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን (አመንኩ ትላለህ) Now? And you had disobeyed [Him] before and were of the corrupters? 10:92 ዛሬማ ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ (ከባሕሩ) እናወጣሃለን (ተባለ)፡፡ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው፡፡ ባመኑ ነበር፡፡ ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን So today We will save you in body that you may be to those who succeed you a sign. And indeed, many among the people, of Our signs, are heedless 10:93 የእስራኤልንም ልጆች ምስጉንን ስፍራ በእርግጥ አሰፈርናቸው፡፡ ከመልካም ሲሳዮችም ሰጠናቸው፡፡ ዕውቀትም (ቁርኣን) እስከመጣቸው ድረስ አልተለያዩም፡፡ ጌታህ በርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡ And We had certainty settled the Children of Israel in an agreeable settlement and provided them with good things. And they did not differ until [after] knowledge had come to them. Indeed, your Lord will judge between them on the Day of Resurrection concerning that over which they used to differ 10:94 ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፡፡ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን፡፡ So if you are in doubt, [O Muhammad], about that which We have revealed to you, then ask those who have been reading the Scripture before you. The truth has certainly come to you from your Lord, so never be among the doubters. 10:95 ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና፡፡ And never be of those who deny the signs of Allah and [thus] be among the losers. 10:96 እነዚያ በእነርሱ ላይ የጌታህ ቃል የተረጋገጠባቸው አያምኑም፡፡ Indeed, those upon whom the word of your Lord has come into effect will not believe, 10:97 ተዓምር ሁሉ ብትመጣላቸውም አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ ድረስ (አያምኑም)፡፡ Even if every sign should come to them, until they see the painful punishment. 10:98 (ከዩኑስ በፊት ካለፉት ከተሞች) ያመነችና እምነትዋ የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም ግን የዩኑስ ሕዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው፡፡ Then has there not been a [single] city that believed so its faith benefited it except the people of Jonah? When they believed, We removed from them the punishment of disgrace in worldly life and gave them enjoyment for a time. 10:99 ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር፡፡ ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን And had your Lord willed, those on earth would have believed - all of them entirely. Then, [O Muhammad], would you compel the people in order that they become believers? 10:100 ለማንኛዋም ነፍስ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ልታምን (ችሎታ) የላትም፡፡ (አላህ ለከፊሎቹ እምነትን ይሻል)፡፡ በእነዚያም በማያውቁት ላይ ርክሰትን ያደርጋል፡፡ And it is not for a soul to believe except by permission of Allah , and He will place defilement upon those who will not use reason. 10:101 «በሰማያትና በምድር ያለውን (ተዓምር) ተመልከቱ» በላቸው፡፡ ተዓምራቶችና አስፈራሪዎችም ለማያምኑ ሕዝቦች አይጠቅሙም፡፡ Say, Observe what is in the heavens and earth. But of no avail will be signs or warners to a people who do not believe 10:102 የእነዚያን ከእነሱ በፊት ያለፉትን ሕዝቦች ቀኖች ብጤ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን «ተጠባበቁ፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው፡፡ So do they wait except for like [what occurred in] the days of those who passed on before them? Say, Then wait; indeed, I am with you among those who wait. 10:103 ከዚያም መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን እናድናለን፡፡ እንደዚሁም ምእምናንን (ከጭንቅ ሁሉ) እናድናለን፡፡ (ይህ) በእኛ ላይ ተረጋገጠ፡፡ Then We will save our messengers and those who have believed. Thus, it is an obligation upon Us that We save the believers 10:104 «እናንተ ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም፡፡ ግን ያንን የሚገድላችሁን አላህን እገዛለሁ፡፡ ከምእምናን እንድሆንም ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡ Say, [O Muhammad], O people, if you are in doubt as to my religion - then I do not worship those which you worship besides Allah ; but I worship Allah , who causes your death. And I have been commanded to be of the believers 10:105 ፊትህንም (ወደ ቀጥታ) ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁን፡፡ And [commanded], Direct your face toward the religion, inclining to truth, and never be of those who associate others with Allah ; 10:106 «ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትገዛ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)፡፡ And do not invoke besides Allah that which neither benefits you nor harms you, for if you did, then indeed you would be of the wrongdoers. 10:107 አላህም ጉዳትን ቢያደርስብህ ከእርሱ ሌላ ለእርሱ ገላጭ የለውም፡፡ በጎንም ነገር ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ የለም፡፡ ከባሮቹ የሚሻውን በእርሱ ይለይበታል፡፡ እርሱም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ And if Allah should touch you with adversity, there is no remover of it except Him; and if He intends for you good, then there is no repeller of His bounty. He causes it to reach whom He wills of His servants. And He is the Forgiving, the Merciful 10:108 «እናንተ ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ (በእርሱ) የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በራሱ ላይ ነው፡፡ እኔም በእናንተ ላይ ተጠባበቂ አይደለሁም» በላቸው፡፡ Say, O mankind, the truth has come to you from your Lord, so whoever is guided is only guided for [the benefit of] his soul, and whoever goes astray only goes astray [in violation] against it. And I am not over you a manager. 10:109 ወዳንተም የሚወረደውን ነገር ተከተል፡፡ አላህም (በነሱ ላይ) እስከሚፈርድ ድረስ ታገስ፡፡ እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነው፡፡ And follow what is revealed to you, [O Muhammad], and be patient until Allah will judge. And He is the best of judges. 11:1 አ.ለ.ረ. (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርአን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰከኩ፣ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፤ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው። Alif, Lam, Ra. [This is] a Book whose verses are perfected and then presented in detail from [one who is] Wise and Acquainted. 11:2 (እንዲህ በላቸው) ፦ አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ እኔ ለናንተ ከርሱ (የተላክሁ) አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ። [Through a messenger, saying], Do not worship except Allah . Indeed, I am to you from Him a warner and a bringer of good tidings, 11:3 ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፤ ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ፤ እስከ ተወሰነም ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋልና፤ የትሩፋትንም ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳውን) ይሰጠዋል፤ ብትሸሹም እኔ በናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ። And [saying], Seek forgiveness of your Lord and repent to Him, [and] He will let you enjoy a good provision for a specified term and give every doer of favor his favor. But if you turn away, then indeed, I fear for you the punishment of a great Day. 11:4 መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። To Allah is your return, and He is over all things competent. 11:5 ንቁ፣ እነሱ ከርሱ (ከአላህ) ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ፤ ንቁ ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትን የሚገልጹትንም ሁሉ ያውቃል፤ እርሱ በደረቶች ውስ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነውና። Unquestionably, they the disbelievers turn away their breasts to hide themselves from Him. Unquestionably, [even] when they cover themselves in their clothing, Allah knows what they conceal and what they declare. Indeed, He is Knowing of that within the breasts.
Posted on: Tue, 08 Jul 2014 22:32:57 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015