ጁዝ 27፦ ከሱረቱል አዝ -ዛሪያት 31 እስከ - TopicsExpress



          

ጁዝ 27፦ ከሱረቱል አዝ -ዛሪያት 31 እስከ ሱረቱል አል-ሐዲድ 29 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። 51:31 እላንተ መልክተኞች ሆይ ታዲያ ነገራችሁ ምንድነው? አላቸው። [Abraham] said, Then what is your business [here], O messengers? 51:32 (እነርሱም)አሉ ፦ እኛ ወደ አመጠኞች ሕዝቦች ተልከናል። They said, Indeed, we have been sent to a people of criminals 51:33 በነርሱ ላይ ከጭቃ የሆኑን ደንጊያዎች ልንለቅባቸው (ተላክን)። To send down upon them stones of clay, 51:34 በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ (በየስማቸው)ምልክት የተደረገባት ስትሆን። Marked in the presence of your Lord for the transgressors. 51:35 ከምእመናንም፤ በርሷ (በከተማቸው)ውስጥ የነበሩትን አወጣን። So We brought out whoever was in the cities of the believers. 51:36 በውስጧም ከሙስሊሞች ከአንድ ቤት (ቤተሰቦች) በስተቀር አላገኘንም። And We found not within them other than a [single] house of Muslims. 51:37 በውስጧም ለነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን። And We left therein a sign for those who fear the painful punishment. 51:38 በሙሳም(ወሬ) ውስጥ ወደ ፈርዖን በግልፅ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)። And in Moses [was a sign], when We sent him to Pharaoh with clear authority. 51:39 ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም (ከእምነት) ዞረ፤ (እርሱ) ድግምተኛ ወይም እብድ ነው አለም። But he turned away with his supporters and said, A magician or a madman. 51:40 እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው፤ እርሱ ተወቃሽ ሲሆን በባሕር ውስጥ ጣልናቸው። So We took him and his soldiers and cast them into the sea, and he was blameworthy. 51:41 በዓድም በነሱ ላይ መካንን ነፍስ በላክን ጊዜ (ምልክት አለ)። And in Aad [was a sign], when We sent against them the barren wind. 51:42 በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛውንም ነገር እንደበሰበሰ አጥንት ያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወውም። It left nothing of what it came upon but that it made it like disintegrated ruins. 51:43 በሠሙድም ለነርሱ እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ በተባሉ ጊዜ (ምልክት አለ)። And in Thamud, when it was said to them, Enjoy yourselves for a time. 51:44 ከጌታቸው ትእዛዝም ኮሩ፤ እነርሱም እያዩ ጩኸት ያዘቻቸው። But they were insolent toward the command of their Lord, so the thunderbolt seized them while they were looking on. 51:45 መቆምን ምንም አልቻሉም፤ የሚረዱም አልነበሩም። And they were unable to arise, nor could they defend themselves. 51:46 የኑሕንም ሕዝቦች ከዚህ በፊት (አጠፋን)፤ እነርሱ አመጠኞች ሕዝቦች ነበሩና። And [We destroyed] the people of Noah before; indeed, they were a people defiantly disobedient. 51:47 ሰማይንም በኀይል ገነባናት፤ እኛም በርግጥ ቻዮች ነን። And the heaven We constructed with strength, and indeed, We are [its] expander. 51:48 ምድርንም ዘረጋናት፤ ምን ያማርንም ዘርጊዎች (ነን!) And the earth We have spread out, and excellent is the preparer. 51:49 ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ ዓይነትን ፈጠርን፤ And of all things We created two mates; perhaps you will remember. 51:50 ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለናንተ ከርሱ ግልፅ አስጠንቃቂ ነኝና (በላቸው)። So flee to Allah . Indeed, I am to you from Him a clear warner. 51:51 ከአላህም ጋር ሌላ አምላክ አታድርጉ፤ እኔ ለናንተ ከርሱ (የተላክሁ) ግልጽ አስፈራሪ ነኝና። And do not make [as equal] with Allah another deity. Indeed, I am to you from Him a clear warner. 51:52 (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ እነዚያን ከርሱ በፊት የነበሩትን ከመልክተኛ ማንም አልመጣቸውም፣ (እርሱ) ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው ያሉ ቢሆኑ እንጂ። Similarly, there came not to those before them any messenger except that they said, A magician or a madman. 51:53 በርሱ( በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? አይደለም፤ እነርሱ ጥጋበኞች ሕዝቦች ናቸው። Did they suggest it to them? Rather, they [themselves] are a transgressing people. 51:54 ከነሱም (ክርክር) ዘወር በል፤ (ተዋቸው)፤ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና። So leave them, [O Muhammad], for you are not to be blamed. 51:55 ገሥጽም፤ ግሣጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና። And remind, for indeed, the reminder benefits the believers. 51:56 ጋኔንንና ሰውን ሊገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም። And I did not create the jinn and mankind except to worship Me. 51:57 ከነሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፤ ሊመግቡኝም አልሻም። I do not want from them any provision, nor do I want them to feed Me. 51:58 አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ፣ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው። Indeed, it is Allah who is the [continual] Provider, the firm possessor of strength. 51:59 ለነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ቢጤ (የቅጣት) ፋንታ አላቸው፤ ስለዚህ አያስቸኩሉኝ። And indeed, for those who have wronged is a portion [of punishment] like the portion of their predecessors, so let them not impatiently urge Me. 51:60 ለነዚያም ለካዱት ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዮላቸው። And woe to those who have disbelieved from their Day which they are promised. 52:1 በጡር (ጋራ) እምላለሁ። By the mount 52:2 በተጻፈው መጽሐፍም። And [by] a Book inscribed 52:3 በተዘረጋ ብራና ላይ፤ (በተጻፈው)። In parchment spread open 52:4 በደመቀው ቤትም። And [by] the frequented House 52:5 ከፍ በተደረገው ጣራም። And [by] the heaven raised high 52:6 በተመላው ባሕርም እምላለሁ። And [by] the sea filled [with fire], 52:7 የጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው፤ (የማይቀር ነው)። Indeed, the punishment of your Lord will occur. 52:8 ለርሱ ምንም ገፍታሪ የለውም። Of it there is no preventer 52:9 ሰማይ ብርቱ መዞርን በምትዞርበት ቀን (ይሆናል)። On the Day the heaven will sway with circular motion 52:10 ተራራዎችም መኼድን በሚኼዱበት (ቀን)። And the mountains will pass on, departing - 52:11 ለአስተባባዮች ያን ጊዜ ወዮላቸው። Then woe, that Day, to the deniers, 52:12 ለነዚያ እነርሱ በውሸት ውስጥ የሚጫወቱ ለሆኑት። Who are in [empty] discourse amusing themselves 52:13 ወደ ገሀነም እሳት በኀይል መግገፍተርን በሚግገፈተሩበት ቀን፤ The Day they are thrust toward the fire of Hell with a [violent] thrust, [its angels will say], 52:14 ይህች ያቺ በርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁ እሳት ናት። This is the Fire which you used to deny. 52:15 ይህ (ፊት ትሉ እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን? Then is this magic, or do you not see? 52:16 ግቧት፤ ታገሡም፤ ወይም አትታገሡ በናንተ ላይ እኩል ነው፤ የምትመነዱት፣ ትሠሩት የነበራችሁትን (ፍዳ) ብቻ ነው (ይባላሉ)። [Enter to] burn therein; then be patient or impatient - it is all the same for you. You are only being recompensed [for] what you used to do. 52:17 አላህን ፈሪዎች በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው። Indeed, the righteous will be in gardens and pleasure, 52:18 ጌታቸው በሰጣቸው ፀጋ ተደሳቾች ሆነው፣ (በገነት ውስጥ ናቸው)። የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው። Enjoying what their Lord has given them, and their Lord protected them from the punishment of Hellfire. 52:19 ትሠሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ሆናችሁ ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ) ። [They will be told], Eat and drink in satisfaction for what you used to do. 52:20 በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ሆነው (በገነት ይኖራሉ)። ዓይናማዎች በሆኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን። They will be reclining on thrones lined up, and We will marry them to fair women with large, [beautiful] eyes. 52:21 እነዚያም ያመኑትና ዝርያቸውም በ እምነት የተከተልቻቸው፣ ዝርያቸውን በነሱ እናስጠጋለን፤ ከሥራቸውም ምንም አናጎድልባቸውም፤ ሰው ሁሉ በሰራው ሥራ ተያዢ ነው። And those who believed and whose descendants followed them in faith - We will join with them their descendants, and We will not deprive them of anything of their deeds. Every person, for what he earned, is retained. 52:22 ከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን። And We will provide them with fruit and meat from whatever they desire. 52:23 በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ፤ በውስጧ ውድቅ ንግንግርና መውወንጀልም የለም። They will exchange with one another a cup [of wine] wherein [results] no ill speech or commission of sin. 52:24 ለነርሱም የሆኑ ወጣቶች፣ ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በነርሱ ላይ (ለማሳለፍ) ይዘዋወራሉ። There will circulate among them [servant] boys [especially] for them, as if they were pearls well-protected. 52:25 የሚጠያየቁ ሆነውም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል። And they will approach one another, inquiring of each other. 52:26 እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ (ከቅጣት) ፈሪዎች ነበርን ይላሉ። They will say, Indeed, we were previously among our people fearful [of displeasing Allah ]. 52:27 አላህም በኛ ላይ ለገሰ፤ የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን። So Allah conferred favor upon us and protected us from the punishment of the Scorching Fire. 52:28 እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን፤ እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና (ይላሉ) ። Indeed, we used to supplicate Him before. Indeed, it is He who is the Beneficent, the Merciful. 52:29 (ሰዎችን) አስታውስም፤ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም ዕብድም አይደለህም። So remind [O Muhammad], for you are not, by the favor of your Lord, a soothsayer or a madman. 52:30 ይልቁንም የሞትን አደጋ በርሱ የምንጠባበቅበት የሆነ ባለ ቅኔ ነው ይላሉን? Or do they say [of you], A poet for whom we await a misfortune of time? 52:31 ተጠባበቁ፤ እኔም ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ በላቸው። Say, Wait, for indeed I am, with you, among the waiters. 52:32 አእምሮዎቻቸው በዚህ ያዟቸዋልን? አይደለም በውነቱ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናቸው። Or do their minds command them to [say] this, or are they a transgressing people? 52:33 ወይም ቀጠፈው ይላሉን? አይደለም፤ በውነቱ አያምኑም። Or do they say, He has made it up? Rather, they do not believe. 52:34 እውነተኞችም ቢሆኑ መሰሉ የሆነ ንግግር ያምጡ። Then let them produce a statement like it, if they should be truthful. 52:35 ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን? Or were they created by nothing, or were they the creators [of themselves]? 52:36 ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም። Or did they create the heavens and the earth? Rather, they are not certain. 52:37 ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነሱ አሸናፊዎች ናቸውን? Or have they the depositories [containing the provision] of your Lord? Or are they the controllers [of them]? 52:38 ወይስ ለነሱ በርሱ ላይ (ከሰማይ) የሚያዳምጡበት መሰላል አላቸውን? አድማጫቸውም (ሰማሁ ቢል) ግልጽን አስረጅ ያምጣ። Or have they a stairway [into the heaven] upon which they listen? Then let their listener produce a clear authority. 52:39 ወይስ ለርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን? ለናንተም ወንዶች አሏችሁን? Or has He daughters while you have sons? 52:40 ወይስ ዋጋን ትጠይቃላችሁን? ስለዚህ እነሱ ከዕዳው የተከበዱ ናቸውን? Or do you, [O Muhammad], ask of them a payment, so they are by debt burdened down? 52:41 ወይስ ሩቅ ሚስጢር እነሱ ዘንድ ነውን? ስለዚህ እነሱ ይጽፋሉን? Or have they [knowledge of] the unseen, so they write [it] down? 52:42 ወይስ ተንኮልን (ባንተ) ይሻሉን? እነዚያ የካዱት እነሱ በተንኮል ተሸናፊዎች ናቸው። Or do they intend a plan? But those who disbelieve - they are the object of a plan. 52:43 ወይስ ለነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ አላቸውን? አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ። Or have they a deity other than Allah ? Exalted is Allah above whatever they associate with Him. 52:44 ከሰማይም ቁራጭን (በነሱ ላይ) ወዳቂ ሆኖ ቢያዩ ኖሮ ይህ የተደራረበ ደመና ነው ይሉ ነበር። And if they were to see a fragment from the sky falling, they would say, [It is merely] clouds heaped up. 52:45 ያንንም በርሱ የሚግገደሉበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው። So leave them until they meet their Day in which they will be struck insensible - 52:46 ተንኮላቸው ከነርሱ ምንንም የማይጠቅማቸውንና እነሱም የማይረዱበትን ቀን (እስከሚገናኙ ተዋቸው)። The Day their plan will not avail them at all, nor will they be helped. 52:47 ለነዚያ ለበደሉትም ከዚህ ሌላ ቅርብ ቅጣት አላቸው፤ (1) ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም። And indeed, for those who have wronged is a punishment before that, but most of them do not know. 52:48 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፤ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፤ ጌታህንም በምትንነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው። And be patient, [O Muhammad], for the decision of your Lord, for indeed, you are in Our eyes. And exalt [ Allah ] with praise of your Lord when you arise. 52:49 ከሌሊቱም አወድሰው፤ በከዋክብት መደበቂያ ጊዜም አወድሰው (እንጋት ላይ አወድሰው)። And in a part of the night exalt Him and after [the setting of] the stars. 53:1 በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ። By the star when it descends, 53:2 ነቢያችሁ፣ (ሙሀመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም። Your companion [Muhammad] has not strayed, nor has he erred, 53:3 ከልብ ወለድም አይናገርም። Nor does he speak from [his own] inclination. 53:4 እርሱ (ንግግሩ) የሚወረድ ራዕይ እንጂ ሌላ አይደለም። It is not but a revelation revealed, 53:5 ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው። Taught to him by one intense in strength - 53:6 የዕውቀት ባለቤት የሆነው (አስተማረው በተፈጥሮ ቅርጹ ሆኖ በአየር ላይ) ተደላደለም። One of soundness. And he rose to [his] true form 53:7 እርሱ በላይኛው አድማስ ሆኖ። While he was in the higher [part of the] horizon. 53:8 ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም። Then he approached and descended 53:9 (ከርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል፣ ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ሆነም። And was at a distance of two bow lengths or nearer. 53:10 ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ። And he revealed to His Servant what he revealed. 53:11 (ነቢዩ በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም። The heart did not lie [about] what it saw. 53:12 ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን? So will you dispute with him over what he saw? 53:13 በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል። And he certainly saw him in another descent 53:14 በመጨረሻይቱ ቁርቁራ (1) አጠገብ፤ At the Lote Tree of the Utmost Boundary - 53:15 እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትሆን። Near it is the Garden of Refuge - 53:16 ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)። When there covered the Lote Tree that which covered [it]. 53:17 ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፤ ወሰንም አላለፈም። The sight [of the Prophet] did not swerve, nor did it transgress [its limit]. 53:18 ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ። He certainly saw of the greatest signs of his Lord. 53:19 አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? So have you considered al-Lat and al-Uzza? 53:20 ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (1) (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?) And Manat, the third - the other one? 53:21 ለናንተ ወንድ ለርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን? Is the male for you and for Him the female? 53:22 ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት። That, then, is an unjust division 53:23 እነርሱ፣ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም። አላህ በርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፤ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲሆኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚያዛነብሉትን እንጅ ሌላ አይከተሉም። They are not but [mere] names you have named them - you and your forefathers - for which Allah has sent down no authority. They follow not except assumption and what [their] souls desire, and there has already come to them from their Lord guidance. 53:24 ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን? Or is there for man whatever he wishes? 53:25 መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው። Rather, to Allah belongs the Hereafter and the first [life]. 53:26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢሆን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም። And how many angels there are in the heavens whose intercession will not avail at all except [only] after Allah has permitted [it] to whom He wills and approves. 53:27 እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት፣ መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ። Indeed, those who do not believe in the Hereafter name the angels female names, 53:28 ለነሱም በርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፤ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፤ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም። And they have thereof no knowledge. They follow not except assumption, and indeed, assumption avails not against the truth at all 53:29 ከግሣጼያችንም (ከቁርአን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)። So turn away from whoever turns his back on Our message and desires not except the worldly life. 53:30 ይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ዲካቸው ነው፤ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፤ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው። That is their sum of knowledge. Indeed, your Lord is most knowing of who strays from His way, and He is most knowing of who is guided 53:31 በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው። እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊቀጣ እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (የጠመመውንና የቀናውን ያውቃል)። And to Allah belongs whatever is in the heavens and whatever is in the earth - that He may recompense those who do evil with [the penalty of] what they have done and recompense those who do good with the best [reward] - 53:32 (እነርሱ) እነዚያ የኃጢያትን ታላላቆችና አስጠያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፤ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው። ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፤ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በሆናችሁ ጊዜ፣ እርሱ በናንተ (ሁነታ) ዐዋቂ ነው። ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው። Those who avoid the major sins and immoralities, only [committing] slight ones. Indeed, your Lord is vast in forgiveness. He was most knowing of you when He produced you from the earth and when you were fetuses in the wombs of your mothers. So do not claim yourselves to be pure; He is most knowing of who fears Him 53:33 ያንን (ከእምነት) የዞረውን አየህን? Have you seen the one who turned away 53:34 ጥቂትን የሰጠውንና ያቋረጠውንም፣ (አየህን?) And gave a little and [then] refrained? 53:35 የሩቁ ሚስጢር ዕውቀት እርሱ ዘንድ አለን? ስለዚህ እርሱ ያያልን? Does he have knowledge of the unseen, so he sees? 53:36 ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሁፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? Or has he not been informed of what was in the scriptures of Moses 53:37 በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም ጽሁፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) And [of] Abraham, who fulfilled [his obligations] - 53:38 (እርሱም ኃጢአት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም። That no bearer of burdens will bear the burden of another 53:39 ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም። And that there is not for man except that [good] for which he strives 53:40 ሥራውም ሁሉ ወደፊት ይታያል። And that his effort is going to be seen - 53:41 ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል። Then he will be recompensed for it with the fullest recompense 53:42 መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው። And that to your Lord is the finality 53:43 እነሆ እርሱም አስሳቀ፤ አስለቀሰም። And that it is He who makes [one] laugh and weep 53:44 እነሆ እርሱም ገደለ፤ አስነሳም። And that it is He who causes death and gives life 53:45 እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድና ሴትን ፈጠረ። And that He creates the two mates - the male and female - 53:46 ከፍትወት ጠብታ (በማኅፀን ውስጥ) በምትፈስስ ጊዜ፤ From a sperm-drop when it is emitted 53:47 የኋለኛይቱም ማስነሳት በርሱ ላይ ነው። And that [incumbent] upon Him is the next creation 53:48 እነሆ እርሱም አከበረ፤ ጥሪተኛም አደረገ። And that it is He who enriches and suffices 53:49 እነሆ እርሱም የሺዕራ(1) ጌታ ነው። And that it is He who is the Lord of Sirius 53:50 እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል። And that He destroyed the first [people of] Aad 53:51 ሠሙድንም፣ (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም። And Thamud - and He did not spare [them] - 53:52 በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፤ እነሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነሱ ነበሩና። And the people of Noah before. Indeed, it was they who were [even] more unjust and oppressing. 53:53 የተገለበጠችውን ከተማ ደፋ። And the overturned towns He hurled down 53:54 ያለበሳትንም አለበሳት። And covered them by that which He covered. 53:55 ከጌታህም ጸጋዎች በትየኛው ትጠራጠራለህ? Then which of the favors of your Lord do you doubt? 53:56 ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የሆነ አስፈራሪ ነው። This [Prophet] is a warner like the former warners. 53:57 ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች። The Approaching Day has approached. 53:58 ለርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም። Of it, [from those] besides Allah , there is no remover. 53:59 ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን? Then at this statement do you wonder? 53:60 ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን? And you laugh and do not weep 53:61 እናንተ ዘንጊዎች ናችሁ። While you are proudly sporting? 53:62 ለአላህ ስገዱ ተገዙትም። So prostrate to Allah and worship [Him]. 54:1 ስዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፤ The Hour has come near, and the moon has split [in two]. 54:2 ታምርንም ቢያዩ (ከአምነት) ይዞራሉ (ይህ) ዘውታሪ ደግመት ነውም ይላሉ And if they see a miracle, they turn away and say, Passing magic. 54:3 አስተባበሉም፤ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፤ ነገርም ሁሉ ( ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው:: And they denied and followed their inclinations. But for every matter is a [time of] settlement. 54:4 ከዜናዎችም በርሱ ውስጥ መገሠጥ ያለበት ነገር በእርግጥ መታላቸው:: And there has already come to them of information that in which there is deterrence - 54:5 ሙሉ የሆነች ጥበብ (መጣቻቸው) ግን አስፈራሪዎቹ አይብቃቁም:: Extensive wisdom - but warning does not avail [them]. 54:6 ከነርሱም ዙር፡ ጠሪው (መልአክ) ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን (አስታውስ)። So leave them, [O Muhammad]. The Day the Caller calls to something forbidding, 54:7 ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ሆነው ፍፁም የተበተነ አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወሉ:: Their eyes humbled, they will emerge from the graves as if they were locusts spreading, 54:8 ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎች ቸካዮች ሆነው (ይወጣሉ) ከሐዲዎች (ያን ጊዜ ምን ይላሉ?) ይህ ብርቱ ቀን ነው ይላሉ፤ Racing ahead toward the Caller. The disbelievers will say, This is a difficult Day. 54:9 ከነሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች። ባሪያችንንም (ኑሕን) አስተባበሉ፤ እብድ ነውም አሉ፤ ተገለመጠም። The people of Noah denied before them, and they denied Our servant and said, A madman, and he was repelled. 54:10 ጌታውንም እኔ የተሽነፍኩ ነኝና እርዳኝ ሲል ጠራ። So he invoked his Lord, Indeed, I am overpowered, so help. 54:11 ወዲያዉም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን፡ Then We opened the gates of the heaven with rain pouring down 54:12 የምድርንም ምንጮች አፈነዳን፤ ውሃውም (የስማይና የምድሩ) በእርግጥ የተወሰነ ሁኔታ ላይ ተገናኘ:: And caused the earth to burst with springs, and the waters met for a matter already predestined 54:13 ባለ ሳንቃዎችና ባለ ሚስማሮች በሆነችም ታንኳ ላይ ጫነው፤ And We carried him on a [construction of] planks and nails, 54:14 በጥበቃችን ስር ሆና ተንሻለላለች። ተክዶ ለነበረው ስው ምንዳ (ይሕንን ሠራን)። Sailing under Our observation as reward for he who had been denied 54:15 ታምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት፤ ከተገሣጭም አለልን? And We left it as a sign, so is there any who will remember? 54:16 ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ? And how [severe] were My punishment and warning. 54:17 ቁርአንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው ተገንዛቢም አልለን? And We have certainly made the Quran easy for remembrance, so is there any who will remember? 54:18 ዓድ አስተባበለች ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ! Aad denied; and how [severe] were My punishment and warning. 54:19 እኛ በነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በኾነ ቀን በቫይል የምትንሻሻ ነፋስን ላክንባቸው:: Indeed, We sent upon them a screaming wind on a day of continuous misfortune, 54:20 ስዎችን ልክ ከሥሮቻቸው የተጐለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው (ከተደበቁበት) ትነቅላቸዋለች። Extracting the people as if they were trunks of palm trees uprooted 54:21 ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ? And how [severe] were My punishment and warning. 54:22 ቁርአንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው ተገሣጭም አለን? And We have certainly made the Quran easy for remembrance, so is there any who will remember? 54:23 ሠሙድ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች። Thamud denied the warning 54:24 ከኛ የሆነን አንድን ስው እንከተለዋለን? እኛ ያን ጊዜ በስሕተትና በዕብደት ውስጥ ነን አሉ:: And said, Is it one human being among us that we should follow? Indeed, we would then be in error and madness. 54:25 ከኛ መካከል በርሱ ላይ (ብቻ) ማስገንዘቢያ (ራእይ) ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ዉሽታም ኩሩ ነው (አሉ)። Has the message been sent down upon him from among us? Rather, he is an insolent liar. 54:26 ዉሽታሙ፤ ኩሩው ማን እንደሆነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ:: They will know tomorrow who is the insolent liar. 54:27 እኛ ሴት ግመልን ለነርሱ መፈተኛ ትሆን ዘንድ ላኪዎች ነን፤ ተጠባበቃቸውም፤ ታገሥም:: Indeed, We are sending the she-camel as trial for them, so watch them and be patient. 54:28 ውሃውም በመካከላቸው የተከፈለ መሆኑን ንገራቸው፤ ከውሃ የሆነ ፋንታ ሁሉ (ተረኞቹ) የሚጣዱት ነው:: And inform them that the water is shared between them, each [day of] drink attended [by turn]. 54:29 ጓደኛቸውንም ጠሩ፤ ወዲያውም (ስይፍን) ተቀበለ፤ ወጋትም :: But they called their companion, and he dared and hamstrung [her]. 54:30 ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ? And how [severe] were My punishment and warning. 54:31 እኛ፤ በነሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው፤ (ወዲያውም) ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተስባበረ ርግጋፌ ሆኑ:: Indeed, We sent upon them one blast from the sky, and they became like the dry twig fragments of an [animal] pen. 54:32 ቁርአንንም ለመገንዘብ አገራነው፤ ተገሣጭም አለን? And We have certainly made the Quran easy for remembrance, so is there any who will remember? 54:33 የሉጥ ሕዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበለች:: The people of Lot denied the warning. 54:34 እኛ በነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋሰን ላክን። የሉጥ ቤተስቦች ብቻ ሲቀሩ (እነሱንስ) በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው፤ Indeed, We sent upon them a storm of stones, except the family of Lot - We saved them before dawn 54:35 ከኛ በሆነ ጸጋ (አዳንናቸው) እንደዚሁ ያመስገነን ስው እንመነዳለን :: As favor from us. Thus do We reward he who is grateful. 54:36 ብርቱይቱን አያያዛችንንም በእርግጥ አስጠነቀቃቸው፤ በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ:: And he had already warned them of Our assault, but they disputed the warning. 54:37 ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት ወዲያዉም ዓይኖቻቸውን አበስን፤ ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼንም ቅመሱ (አልናቸው):: And they had demanded from him his guests, but We obliterated their eyes, [saying], Taste My punishment and warning. 54:38 በማለዳም ዘውታሪ የሆነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው:: And there came upon them by morning an abiding punishment. 54:39 ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎችንም ቅመሱ (ተባሉ)። So taste My punishment and warning. 54:40 ቁራአንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፤ ተገሳጭም አልለን ? And We have certainly made the Quran easy for remembrance, so is there any who will remember? 54:41 የፈርዖንንም ቤተስቦች ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጡዋቸው፤ And there certainly came to the people of Pharaoh warning. 54:42 በታምራቶቻችን በሁሏም አሰተባበሉ፤ የብርቱ ቻይንም አያያዝ ያዝናቸው:: They denied Our signs, all of them, so We seized them with a seizure of one Exalted in Might and Perfect in Ability. 54:43 ከሐዲዎቻችሁ ከነዚሃችሁ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለናንተ በመዽሐፎች ውስጥ (የተነገረ ) ነጣነት አላችሁን? Are your disbelievers better than those [former ones], or have you immunity in the scripture? 54:44 ወይስ እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን ይላሉን? Or do they say, We are an assembly supporting [each other]? 54:45 ከምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይመታሉ፤ ጀርባዎችንም ያዞራሉ:: [Their] assembly will be defeated, and they will turn their backs [in retreat]. 54:46 ይልቁንም ስዓቲቱ (ትንሣኤ)ቀጠሮዋቸው ናት፤ ስዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት፤ But the Hour is their appointment [for due punishment], and the Hour is more disastrous and more bitter. 54:47 አመጠኞች በስሕተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው፤ Indeed, the criminals are in error and madness. 54:48 በእሳት ውስጥ በፊቶቻቸው በሚጎተቱበት ቀን የስቀርን (1) መንካት ቅመሱ (ይባላሉ) The Day they are dragged into the Fire on their faces [it will be said], Taste the touch of Saqar. 54:49 እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፤ Indeed, all things We created with predestination. 54:50 ትእዛዛችንም እንደ ዓይን ቅዽበት አንዲት (ቃል) እንጅ ሌላ አይደለም፤ And Our command is but one, like a glance of the eye. 54:51 ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን ተገሣጭም አልለን?፤ And We have already destroyed your kinds, so is there any who will remember? 54:52 የሠሩትንም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ዉስጥ ነው፤ And everything they did is in written records. 54:53 ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተጻፍ ነው፤ And every small and great [thing] is inscribed. 54:54 አላህን ፈሪዎች በአትክልቶችና በወንዞች ዉስጥ ናቸው፤ Indeed, the righteous will be among gardens and rivers, 54:55 (እነሱም ውድቅ ቃልና መወንጀል በሌለበት) በውነት መቀመጫ ዉስጥ ቻይ እሆነው ንጉስ ዘንድ ናቸው:: In a seat of honor near a Sovereign, Perfect in Ability. 55:1 አል-ረሕማን፤ The Most Merciful 55:2 ቁርአንን አስተማረ። Taught the Quran, 55:3 ሰውን ፈጠረ። Created man, 55:4 መናገርን አስተማረው። [And] taught him eloquence 55:5 ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፤ The sun and the moon [move] by precise calculation, 55:6 ሐረግና ዛፍም (ለርሱ) ይሰግዳሉ። And the stars and trees prostrate. 55:7 ሰማይንም አጓናት፤ ትክክለኛነትንም ደነገገ። And the heaven He raised and imposed the balance 55:8 በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ። That you not transgress within the balance. 55:9 መመዘንንም በትክክል መዝኑ፤ ተመዛኙንም አታጕድሉ። And establish weight in justice and do not make deficient the balance. 55:10 ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት። And the earth He laid [out] for the creatures. 55:11 በውስጧ እሸት፥ ባለ ሺፋኖች የሆኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፤ Therein is fruit and palm trees having sheaths [of dates] 55:12 የገለባ ባለቤት የሆነ ቅንጣትም፤ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትሆን) And grain having husks and scented plants. 55:13 (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:14 ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው። He created man from clay like [that of] pottery. 55:15 ጅንንም (1) ከእሳት ከሆነ ነበልባል ፈጠርነው። And He created the jinn from a smokeless flame of fire. 55:16 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:17 የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው። [He is] Lord of the two sunrises and Lord of the two sunsets. 55:18 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:19 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲሆኑ ለቀቃቸው። He released the two seas, meeting [side by side]; 55:20 (እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፤ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፍም፤ Between them is a barrier [so] neither of them transgresses. 55:21 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:22 ሉልና መርጃን ከሁለቱ (2)ይወጣል። From both of them emerge pearl and coral 55:23 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:24 እንደ ጋራዎች ሆነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻላዮቹም፥ (ታንኳዎች) የርሱ ናቸው። And to Him belong the ships [with sails] elevated in the sea like mountains. 55:25 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:26 በርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው። Everyone upon the earth will perish 55:27 የልቅናና የልግሥና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊትም ይቀራል። (አይጠፋም)። And there will remain the Face of your Lord, Owner of Majesty and Honor. 55:28 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:29 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፤ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው። Whoever is within the heavens and earth asks Him; every day He is bringing about a matter 55:30 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:31 እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ፥ ለናንተ (መቆጣጠር) በእርገጥ እናስባለን። = ሆነ ብለን እናስብበታለን ይህ ብርቱ ዛቻ ነው። We will attend to you, O prominent beings. 55:32 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:33 የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፤ በስልጣን እንጅ አትወጡም። (ግን ስልጣን የላሁም)። O company of jinn and mankind, if you are able to pass beyond the regions of the heavens and the earth, then pass. You will not pass except by authority [from Allah ]. 55:34 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:35 በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል ጭስም ይላክባችኋል፤ (ሁለታችሁም) አትረዱምም። There will be sent upon you a flame of fire and smoke, and you will not defend yourselves. 55:36 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:37 ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፥ እንደታረበ ቆዳ በሆነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው )። And when the heaven is split open and becomes rose- colored like oil - 55:38 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? - 55:39 በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢአቱ ገና አይጠየቅም። Then on that Day none will be asked about his sin among men or jinn. 55:40 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:41 ከሐዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ። አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ። The criminals will be known by their marks, and they will be seized by the forelocks and the feet. 55:42 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:43 ይህቺ ያቺ አመጠኞች በርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ) ። This is Hell, which the criminals deny. 55:44 በርሷና በጣም ሞቃት በሆነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ። They will go around between it and scalding water, heated [to the utmost degree]. 55:45 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:46 በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው፥ ሁለት ገነቶች አሉት። But for he who has feared the position of his Lord are two gardens - 55:47 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? - 55:48 የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የሆኑ፥ (ገነቶች አሉት)። Having [spreading] branches. 55:49 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:50 በሁለቱ ውስጥ የሚፈሱ ሁለት ምንጮች አሉ። In both of them are two springs, flowing 55:51 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:52 በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ)አልሉ። In both of them are of every fruit, two kinds 55:53 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:54 የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በሆኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲሆኑ (ይንፈላሰሳሉ)፤ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው። [They are] reclining on beds whose linings are of silk brocade, and the fruit of the two gardens is hanging low. 55:55 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:56 በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጅንም ያልገሠሣቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ። In them are women limiting [their] glances, untouched before them by man or jinni - 55:57 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? - 55:57 ልክ ያቁትና መርጃን (1) ይመስላሉ As if they were rubies and coral. 55:59 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:60 የበጎ ሥራ ዋጋ፥ በጎ እንጅ ሌላ ነውን? Is the reward for good [anything] but good? 55:61 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:62 ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ፥ ሁለት ገነቶች አሉ። And below them both [in excellence] are two [other] gardens - 55:63 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? - 55:64 ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው። Dark green [in color]. 55:65 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:66 በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አሉ። In both of them are two springs, spouting. 55:67 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:68 በውስጣቸው ፍራፍሬ፥ ዘምባባም ሩማንም አልለ። In both of them are fruit and palm trees and pomegranates 55:69 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:70 በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልከ ውቦች (ሴቶች) አልሉ። In them are good and beautiful women - 55:71 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? - 55:72 በድንኳኖች ውስጥ የተጨጐሉ፥ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የሆኑ ናቸው። Fair ones reserved in pavilions - 55:73 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? - 55:74 ከነሱ በፊት፥ ሰውም ጃንም አልገሠሣቸውም። Untouched before them by man or jinni - 55:75 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? - 55:76 በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲሆኑ (ይቀመጣሉ)። Reclining on green cushions and beautiful fine carpets 55:77 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? So which of the favors of your Lord would you deny? 55:78 የግርማና የመክበር ባለቤት የሆነው ጌታህ ስም ተባረከ። Blessed is the name of your Lord, Owner of Majesty and Honor. 56:1 መከራዪቱ በወደቀች ጊዜ። When the Occurrence occurs, 56:2 ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም። There is, at its occurrence, no denial. 56:3 ዝቅ አድራጊና፣ ከፍ አድራጊ ናት። It will bring down [some] and raise up [others]. 56:4 ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ። When the earth is shaken with convulsion 56:5 ተራሮችም መፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በሆኑ ጊዜ)። And the mountains are broken down, crumbling 56:6 የተበተነ ብናኝ በሆኑም ጊዜ And become dust dispersing. 56:7 ሦስት ዓይነቶችም በሆናችሁ ጊዜ፣ (ታዋርዳለች ታነሳለችም)። And you become [of] three kinds: 56:8 የቀኝ ጓዶችም፣ ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው። Then the companions of the right - what are the companions of the right? 56:9 የግራ ጓዶችም፣ ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው። And the companions of the left - what are the companions of the left? 56:10 (ለበጎ ስራ) ቀዳሚዎቹም፣ (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው። And the forerunners, the forerunners - 56:11 እነዚያ፣ ባለሟሎቹ ናቸው። Those are the ones brought near [to Allah ] 56:12 በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲሆኑ። In the Gardens of Pleasure, 56:13 ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው። A [large] company of the former peoples 56:14 ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው። And a few of the later peoples, 56:15 በተታቱ አልጋዎች ላይ ይሆናሉ። On thrones woven [with ornament], 56:16 በርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲሆኑ። Reclining on them, facing each other 56:17 በነሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ። There will circulate among them young boys made eternal 56:18 ከጠጅ ምንጭም፣ በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በነሱ ላይ ይዞራሉ)። With vessels, pitchers and a cup [of wine] from a flowing spring - 56:19 ከርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም። No headache will they have therefrom, nor will they be intoxicated - 56:20 ከሚመርጡት ዓይነት በእሸቶች። And fruit of what they select 56:21 ከሚሹትም በሆነ የበራሪ ሥጋ፣ (ይዞሩባቸዋል)። And the meat of fowl, from whatever they desire. 56:22 አይናማዎች የሆኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው። And [for them are] fair women with large, [beautiful] eyes 56:23 ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የሆኑ። The likenesses of pearls well-protected, 56:24 በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይሆን ዘንድ፣ (ይህንን አደረግንላቸው)። As reward for what they used to do. 56:25 በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም። They will not hear therein ill speech or commission of sin - 56:26 ግን ሰላም መባባልን፣ (ይሰማሉ)። Only a saying: Peace, peace. 56:27 የቀኝ ጓዶችም፣ ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች! The companions of the right - what are the companions of the right? 56:28 በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው። [They will be] among lote trees with thorns removed 56:29 (ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም። And [banana] trees layered [with fruit] 56:30 በተዘረጋ ጥላ ሥርም። And shade extended 56:31 በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም። And water poured out 56:32 ብዙ (ዓይነት) በሆኑ ፍራፍሬዎችም። And fruit, abundant [and varied], 56:33 የማትቋረጥም፣ የማትከለከልም፣ የሆነች። Neither limited [to season] nor forbidden, 56:34 ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም፣ (ሴቶችም፣ መካከል)። And [upon] beds raised high 56:35 እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለነሱ) ፈጠርናቸው። Indeed, We have produced the women of Paradise in a [new] creation 56:36 ደናግሎችም አደረግናቸው። And made them virgins, 56:37 ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች፣ እኩያዎች (አደረግናቸው)። Devoted [to their husbands] and of equal age, 56:38 ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)። For the companions of the right [who are] 56:39 ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው። A company of the former peoples 56:40 ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው። And a company of the later peoples. 56:41 የግራ ጓዶችም፣ ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው። And the companions of the left - what are the companions of the left? 56:42 በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው። [They will be] in scorching fire and scalding water 56:43 ከጥቁር ጭስም በሆነ ጥላ ውስጥ። And a shade of black smoke, 56:44 ቀዝቃዛም መልካምም ያልሆነ። Neither cool nor beneficial 56:45 እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና። Indeed they were, before that, indulging in affluence, 56:46 በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበርና። And they used to persist in the great violation, 56:47 ይሉም ነበሩ ፦ በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በሆን ጊዜ፣ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን? And they used to say, When we die and become dust and bones, are we indeed to be resurrected? 56:48 የፊተኞቹ አባቶቻችንም? And our forefathers [as well]? 56:49 በላቸው ፦ ፊተኞቹም ኋለኞቹም። Say, [O Muhammad], Indeed, the former and the later peoples 56:50 በተወሰነ ቀን ቀጠሮ፣ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው። Are to be gathered together for the appointment of a known Day. 56:51 ከዚያም፣ እናንተ ጠማሞች፣ አስተባባዮች ሆይ፤ Then indeed you, O those astray [who are] deniers, 56:52 ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ። Will be eating from trees of zaqqum 56:53 ከርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ። And filling with it your bellies 56:54 በርሱ ላይም ከፈላ ውኀ ጠጪዎች ናችሁ። And drinking on top of it from scalding water 56:55 የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ቢጤ፣ ጠጪዎች ናችሁ። And will drink as the drinking of thirsty camels. 56:56 ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው። That is their accommodation on the Day of Recompense 56:57 እኛ ፈጠርናችሁ፤ አታምኑምን? We have created you, so why do you not believe? 56:58 (በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁትን? Have you seen that which you emit? 56:59 እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹ ነን። Is it you who creates it, or are We the Creator? 56:60 እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን።እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም። We have decreed death among you, and We are not to be outdone 56:61 ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)። In that We will change your likenesses and produce you in that [form] which you do not know. 56:62 የፊተኛይቱንም አፈጣጠር (1) በእርግጥ አውቃችኋል፤ አትገነዘቡምን? And you have already known the first creation, so will you not remember? 56:63 የምትዘሩትንም አያችሁን? And have you seen that [seed] which you sow? 56:64 እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን? Is it you who makes it grow, or are We the grower 56:65 ብንሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በሆናችሁ ነበር። If We willed, We could make it [dry] debris, and you would remain in wonder, 56:66 እኛ በዕዳ ተያዦች ነን። [Saying], Indeed, we are [now] in debt; 56:67 በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን፣ (ትሉ ነበር)። Rather, we have been deprived. 56:68 ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አያችሁን? And have you seen the water that you drink? 56:69 እናንተ ከደመና አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን? Is it you who brought it down from the clouds, or is it We who bring it down? 56:70 ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደርግነው ነበር። አታመሰግኑምን? If We willed, We could make it bitter, so why are you not grateful? 56:71 ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን? And have you seen the fire that you ignite? 56:72 እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን? Is it you who produced its tree, or are We the producer? 56:73 እኛ ለገሃነም ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት። We have made it a reminder and provision for the travelers, 56:74 የታላቁን የጌታህን ስም አወድስ። So exalt the name of your Lord, the Most Great 56:75 በክዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ። Then I swear by the setting of the stars, 56:76 እርሱም ብታውቁ ታላቅ መሐላ ነው And indeed, it is an oath - if you could know - [most] great 56:77 እሱ የከበረ ቁርአን ነው። Indeed, it is a noble Quran 56:78 በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው። In a Register well-protected; 56:79 የተጥራሩት እንጂ ሌላ አይነካውም። None touch it except the purified. 56:80 ከአለማት ጌታ የተወረደ ነው። [Itis] a revelation from the Lord of the worlds. 56:81 በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን? Then is it to this statement that you are indifferent 56:82 ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን? And make [the thanks for] your provision that you deny [the Provider]? 56:83 (ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ። Then why, when the soul at death reaches the throat 56:84 እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትሆኑ። And you are at that time looking on - 56:85 እኛም ግን አታዩም እንጅ ከናንተ ይልቅ ወደርሱ የቀረብን ስንሆን። And Our angels are nearer to him than you, but you do not see - 56:86 የማትዳኙም ከሆናችሁ። Then why do you not, if you are not to be recompensed 56:87 እውነተኞች እንደሆናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም። Bring it back, if you should be truthful? 56:88 (ሟቹ) ከባልሟሎቹ ቢሆንማ። And if the deceased was of those brought near to Allah , 56:89 (ለርሱ) ዕረፍት መልካም ሲሳይም የመጠቀሚያ ገነትም አለው። Then [for him is] rest and bounty and a garden of pleasure. 56:90 ከቀኝ ጓዶችም ቢሆንማ። And if he was of the companions of the right, 56:91 ከቀኝ ጓዶች ስለሆንክ ላንተ ሰላም አልልህ (ይባላል)። Then [the angels will say], Peace for you; [you are] from the companions of the right. 56:92 ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢሆንማ። But if he was of the deniers [who were] astray, 56:93 ከፈላ ውሃ የሆነ መስተንግዶ አለው። Then [for him is] accommodation of scalding water 56:94 በገሃነም መቃጠልም (አለው)። And burning in Hellfire 56:95 ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው። Indeed, this is the true certainty, 56:96 የታላቁን ጌታህን ስም አወድስ። So exalt the name of your Lord, the Most Great. 57:1 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፤ እርሱም ሁሉን አሸናፊው ጥበበኛው ነው። Whatever is in the heavens and earth exalts Allah , and He is the Exalted in Might, the Wise. 57:2 የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፤ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነው። His is the dominion of the heavens and earth. He gives life and causes death, and He is over all things competent. 57:3 እርሱ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ፣ ግልፅም ስውርም ነው፤ እርሱም ነገርን ሁሉ ዐዋቂ ነው። He is the First and the Last, the Ascendant and the Intimate, and He is, of all things, Knowing. 57:4 እርሱ ሰማያትንና ምድርን በ6 ቀናት ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዙፋኑ ላይ (ሥልጣኑ) የተደላደለ ነው፤ በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም የሚወርደውን፣ በርሷም ውስጥ የሚያደርገውን፣ ያውቃል፤ እርሱም የትም ብትሆኑ ከናንተ ጋር ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው። It is He who created the heavens and earth in six days and then established Himself above the Throne. He knows what penetrates into the earth and what emerges from it and what descends from the heaven and what ascends therein; and He is with you wherever you are. And Allah , of what you do, is Seeing. 57:5 የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፤ ነገሮችም (ሁሉ) ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ። His is the dominion of the heavens and earth. And to Allah are returned [all] matters 57:6 ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፤ ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል፤ እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ዐዋቂ ነው። He causes the night to enter the day and causes the day to enter the night, and he is Knowing of that within the breasts. 57:7 በአላህና በመልክተኛው እመኑ፤ (አላህ) በርሱ ተተኪዎች ባደረጋችሁም ገንዘብ ለግሱ፤ እነዚያም ከናንተ ውስጥ ያመኑትና የለገሱት ለርሱ ታላቅ ምንዳ አልላቸው። Believe in Allah and His Messenger and spend out of that in which He has made you successors. For those who have believed among you and spent, there will be a great reward. 57:8 መልክተኛው በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲሆን፣ (ጌታችሁ) ኪዳናችሁንም የያዘባችሁ ሲሆን በአላህ የማታምኑት ለናንተ ምን አላችሁ? የምታምኑ ብትሆኑ፣ (ወደ እምነት ቸኩሉ)። And why do you not believe in Allah while the Messenger invites you to believe in your Lord and He has taken your covenant, if you should [truly] be believers? 57:9 እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ሊያወጣችሁ ያ ግልጾች የሆኑን አንቀጾች በባሪያው ላይ የሚያወርድ ነው፤ አላህም ለናንተ በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነው። It is He who sends down upon His Servant [Muhammad] verses of clear evidence that He may bring you out from darknesses into the light. And indeed, Allah is to you Kind and Merciful. 57:10 የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ መንገድ የምትለግሱትም ለናንተ ምን አልላችሁ? ከናንተ ውስጥ፣ (መካን) ከመክፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው፣ (ከተከፈተች በኋላ ከተከፈተች በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ጋር) አይተካከልም፤ ከነዚያ በኋላ ከለገሡትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው፤ ሁሉንም አላህ መልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል፤ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው። And why do you not spend in the cause of Allah while to Allah belongs the heritage of the heavens and the earth? Not equal among you are those who spent before the conquest [of Makkah] and fought [and those who did so after it]. Those are greater in degree than they who spent afterwards and fought. But to all Allah has promised the best [reward]. And Allah , with what you do, is Acquainted 57:11 ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድር ለርሱም (አላህ) የሚያነባብርለት ሰው ማነው? ለርሱም መልካም ምንዳ አለው። Who is it that would loan Allah a goodly loan so He will multiply it for him and he will have a noble reward? 57:12 ምእምናንና ምእምናትን በስተ ፊቶቻቸው፣ በቀኞቻቸውም ብርሃናቸው የሚሮጥ ሲሆን በምታያቸው ቀን (ምንዳ አልላቸው)። ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትሆኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)። ይህ ራሱ ታላቅ ዕድል ነው። On the Day you see the believing men and believing women, their light proceeding before them and on their right, [it will be said], Your good tidings today are [of] gardens beneath which rivers flow, wherein you will abide eternally. That is what is the great attainment 57:13 መናፍቃንና መናፍቃት፣ ለነዚያ ለአመኑት ተመልከቱን፤ ከብርሃናችሁ እናበራለንና የሚሉበትን ቀን (አስታውስ)፤ ወደ ኋላችሁ ተመለሱ፤ ብርሀንንም ፈልጉ ይባላሉ፤ በመካከላቸውም ለርሱ ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል፤ ግቢው በውስጡ ችሮታ (ገነት) ያለበት፣ ውጭውም ከበኩሉ ስቃይ (እሳት) ያለበት የሆነ (ደጃፍ ባለው አጥር)። On the [same] Day the hypocrite men and hypocrite women will say to those who believed, Wait for us that we may acquire some of your light. It will be said, Go back behind you and seek light. And a wall will be placed between them with a door, its interior containing mercy, but on the outside of it is torment 57:14 ከናንተ ጋር አልነበርንምን? በማለት ይጠሩዋቸዋል፣ እውነት ነው፤ ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ፤ (በነቢዩ አደጋዎችን) ተጠባበቃችሁም፤ ተጠራጠራችሁም፤ የአላህም ት እዛዝ እስከመጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ፤ አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ (መታገሥ) ሸነገላችሁ ይሏቸዋል። The hypocrites will call to the believers, Were we not with you? They will say, Yes, but you afflicted yourselves and awaited [misfortune for us] and doubted, and wishful thinking deluded you until there came the command of Allah . And the Deceiver deceived you concerning Allah. 57:15 ዛሬም ከናንተ ቤዛ አይወሰድም፤ ከነዚያ ከካዱትም መኖሪያችሁ እሳት ናት፤ እርሷ ተገቢያችሁ ናት፤ ምን ትከፋም መመለሻ! (ይሏቸዋል)። So today no ransom will be taken from you or from those who disbelieved. Your refuge is the Fire. It is most worthy of you, and wretched is the destination. 57:16 ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሣጽና ከቁርአንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደተሰጡትና በነርሱ ላይ ጊዜ እንደ ረዘመባቸው፣ ልቦቻቸውም እንደደረቁት ላይሆኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከነርሱም ብዙዎቹ አመጠኞች ናቸው። Has the time not come for those who have believed that their hearts should become humbly submissive at the remembrance of Allah and what has come down of the truth? And let them not be like those who were given the Scripture before, and a long period passed over them, so their hearts hardened; and many of them are defiantly disobedient. 57:17 አላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው የሚያደርጋት መኾኑን ዕወቁ፤ ታውቁ ዘንድ አንቀጾችን ለናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ። Know that Allah gives life to the earth after its lifelessness. We have made clear to you the signs; perhaps you will understand. 57:18 የመጸወቱ ወንዶችና የመጸወቱ ሴቶች ለአላህም መልካምን ብድር ያበደሩ ለነርሱ ይደራረብላቸዋል፤በደሩ ለነርሱ ይደራረብላቸዋል፤ ለነርሱም መልካም ምንዳ አላቸው። Indeed, the men who practice charity and the women who practice charity and [they who] have loaned Allah a goodly loan - it will be multiplied for them, and they will have a noble reward. 57:19 እነዚያም በአላህና በመልክተኞቹ ያመኑት፣ እነዚያ እነሱ በጣም እውነተኞቹ በጌታቸውም ዘንድ መስካሪዎቹ ናቸው፤ ለነርሱ ምንዳቸው ብርሃናቸውም አልላቸው፤ እነዚያም የካዱት በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉት፣ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው። And those who have believed in Allah and His messengers - those are [in the ranks of] the supporters of truth and the martyrs, with their Lord. For them is their reward and their light. But those who have disbelieved and denied Our verses - those are the companions of Hellfire. 57:20 ቅርቢቱ የሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፣ ማጌጫም፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ በገንዘቦችና በልጆችም መፎካከሪያ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መሆንዋን ዕወቁ፤ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅናም ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚሆን ብጤ ናት፤ በመጨረሻዪቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ከአላህም ምሕረትና ውዴታ አልለ፤ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም። Know that the life of this world is but amusement and diversion and adornment and boasting to one another and competition in increase of wealth and children - like the example of a rain whose [resulting] plant growth pleases the tillers; then it dries and you see it turned yellow; then it becomes [scattered] debris. And in the Hereafter is severe punishment and forgiveness from Allah and approval. And what is the worldly life except the enjoyment of delusion 57:21 ከጌታችሁ ወደ ሆነች ምሕረት ወርዷ እንደሰማይና ምድር ወርድ ወደ ሆነችም ገነት ተሽቀዳደሙ፤ ለነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ ላመኑት ተዘጋጅታለች። ይህ የአላህ ችሮታ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፤ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው። Race toward forgiveness from your Lord and a Garden whose width is like the width of the heavens and earth, prepared for those who believed in Allah and His messengers. That is the bounty of Allah which He gives to whom He wills, and Allah is the possessor of great bounty. 57:22 በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጅ፤ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው። No disaster strikes upon the earth or among yourselves except that it is in a register before We bring it into being - indeed that, for Allah , is easy - 57:23 (ይህ ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑ አላህም በሰጣችሁ ነገር (በት ዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው፤ አላህም ኩራተኛን ጉረኛን ሰው አይወድም። In order that you not despair over what has eluded you and not exult [in pride] over what He has given you. And Allah does not like everyone self-deluded and boastful - 57:24 (እነርሱም) እነዚያ የሚሰስቱና ሰዎችንም በሥት የሚያዙ ናቸው፤ (ከውነት) የሚሸሽም ሰው (ጥፋቱ በራሱ ላይ ነው)፤ አላህም እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው። [Those] who are stingy and enjoin upon people stinginess. And whoever turns away - then indeed, Allah is the Free of need, the Praiseworthy. 57:25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደነርሱ አወረድን፤ ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲሆን አወረድን፤ (እንዲጠቀሙበት) አላህም ሃይማኖቱንና መልክተኞቹን በሩቁ ሆኖ የሚረዳውን ሰው ሊያውቅ (ሊገልጽ አወረደው)፤ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና። We have already sent Our messengers with clear evidences and sent down with them the Scripture and the balance that the people may maintain [their affairs] in justice. And We sent down iron, wherein is great military might and benefits for the people, and so that Allah may make evident those who support Him and His messengers unseen. Indeed, Allah is Powerful and Exalted in Might. 57:26 ኑሕን፣ ኢብራሒምንም በእርግጥ ላክን፤ በዘሮቻቸውም ውስጥ ነቢይነትንና መጽሐፎችን አደረግን፤ ከነሱም ቅን አለ፤ ከነሱም ብዙዎች አመጠኞች ናቸው። And We have already sent Noah and Abraham and placed in their descendants prophethood and scripture; and among them is he who is guided, but many of them are defiantly disobedient. 57:27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን የመርየምን ልጅ ኢሳንም አስከተልን፤ ኢንጅልንም ሰጠነው፤ በነዚያም በተከተሉት (ሰዎች) ልቦች ውስጥ መለዘብንና እዝነትን አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና አደረግን፤ በነርሱ ላይ (ምንኩስናን) አልጻፍናትም፤ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ (ፈጠሩዋት)፤ ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም፤ ከነሱም ለነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፤ ከነሱም ብዙዎቹ አመጠኞች ናቸው። Then We sent following their footsteps Our messengers and followed [them] with Jesus, the son of Mary, and gave him the Gospel. And We placed in the hearts of those who followed him compassion and mercy and monasticism, which they innovated; We did not prescribe it for them except [that they did so] seeking the approval of Allah . But they did not observe it with due observance. So We gave the ones who believed among them their reward, but many of them are defiantly disobedient. 57:28 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ በመልክተኛውም እመኑ፤ ከችሮታው ሁለትን ክፍሎች ይሰጣችኋልና፤ ለናንተም በርሱ የምትኼዱበት የሆነ ብርሃንን ያደርግላችኋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነው። O you who have believed, fear Allah and believe in His Messenger; He will [then] give you a double portion of His mercy and make for you a light by which you will walk and forgive you; and Allah is Forgiving and Merciful. 57:29 (ይህም) የመጽሐፉ ሰዎች ከአላህ ችሮታ በምንም ላይ የማይችሉ መሆናቸውን ችሮታም በአላህ እጅ ነው፤ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል ማለትን፣ እንዲያውቁ ነው፤ አላህም ታላቅ የችሮታ ባለቤት ነው። [This is] so that the People of the Scripture may know that they are not able [to obtain] anything from the bounty of Allah and that [all] bounty is in the hand of Allah ; He gives it to whom He wills. And Allah is the possessor of great bounty.
Posted on: Thu, 24 Jul 2014 23:18:50 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015