5 Greatest Group Stage Upsets in World Cup History ... See at ... - TopicsExpress



          

5 Greatest Group Stage Upsets in World Cup History ... See at ... diretu.be/642752 | በአለም ዋንጫ ታሪክ 5ት አስገራሚ የምድብ ጨዋታ ያልተጠበቁ ውጤቶች 5፣ ስፔን 0 ስዊዘርላንድ 1 (2010) የአውሮፓ ሻምፒዮናዋ ስፔን በ2010 የደቡብ አፍሪካ አለም ዋንጫ የሁሉንም ዋንጫ ታነሳለች የሚል ግምት አግኝታ ደቡብ አፍሪካ ብትገባም በመክፈቻ ጨዋታ በስዊዘርላንድ የደረሰባት የመክፈቻ ጨዋታ የአንድ ለዜሮ ሽንፈት በርካቶችን አስደነግጦ ነበር፡፡ ሆኖም የስፔን የሽንፈት ጅሟሮ ብዙም አልቆየም በቀጣይ ጨዋታ ሁንዱራስን፣ ቺሊን፣ ፖርቹጋልን፣ ፓራጉዋይን እና ጀርመንን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሳለች፡፡ በፍጻሜውም ኔዘርላንድን በተጨማሪ ሰአት አሸንፋ የ2010 የአለም ዋንጫ አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡ 4፣ ፈረንሳይ 0 ሴኔጋል 1 (2002) በ1998 የአለም ዋንጫን ያሸነፈችው ፈረንሳይ በ2000 የአውሮፓ ዋንጫንም በማንሳት አለምን አስገረመች ለ2002 ኮሪያ ጃፓን አለም ዋንጫ ብዙ ግምት ተሰጥቶአት ብትደርስም በመክፈቻው ጨዋታ ገና ከጅምሩ በአፍሪካዋ ሀገር ሴኔጋል በፓፓ ቡፓ ዲዩፕ ግብ ተሸነፈች ፈረንሳይ ከምድቡ እንኩዋን ማለፍ ሳትችል ተሰናበተች፡፡ 3፣ ጣሊያን 0 ሰሜን ኮሪያ 1 (1966) በ1966 አለም ዋንጫ ለእንግሊዞች በተለየ መልኩ የሚታወስ ቢሆንም በውድድሩ የተገኙት የሰሜን ኮሪያ ቡድንም ትዝታቸው ዘላለማዊ ነው፡፡ በውድድሩ በሶቪየት ህብረት 3ለ0 ተሸንፈው ከቺሊ 1ለ1 የተለያዩት ሰሜን ኮሪያውያን የመጀመሪያ የአለም ዋንጫ ተሳትፎአቸው በጊዜ ተሰናበቱ ተብሎ ቢገመትም ጣሊያንን አንድ ለዜሮ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በቀጣይ ጨዋታ በፖርቹጋል 5ለ3 ቢሸነፉም አለምን አስገርመው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ 2፣ አርጀንቲና 0 ካሜሮን 1 (1990) ዲያጎ ማራዶናን የያዘው የአርጀንቲና ቡድን ከነክብሩ ነበር ጣሊያን ለ1990 የአለም ዋንጫ የተገኘው አጀማመራቸው አስገራሚ ነበር፡፡ የማራዶና ቡድን በመክፈቻው በሳንሴሮ የገጠመው አፍሪካዊቷን ካሜሮንን ሲሆን በዘጠኝ ሰው የተጫወተው የካሜሮን ቡድን አንድ ለዜሮ በማሸነፍ የአለም ዋንጫ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቦአል፡፡ 1፣ ዩናይትድ ስቴትስ 1 እንግሊዝ 0 (1950) ወጤቱ በበርካቶች በተለየ መልኩ ይታወሳል፣ በ1950 እንግሊዝ በአሜሪካ ተሸነፈች ማለት በአሜሪካ ምድር ተአምር ካለተፈተረ የሚሆን ነገር አይደለም ለእንግሊዛውያን ደግሞ ብሄራዊ ውርደት ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ በ1950 ከየትኛውም ሀገር በላይ ለዋንጫው የተለየ ግምት ተሰጥቶአት የነበረቸው እንግሊዝ ስትሆን አሜሪካ ደግሞ ለቁጥር ማሟያ የገባች ሀገር ነገር ግን የጆ ጋትየንስ ግብ ለአሜሪካ የማይታመን ድል አስመዘገበች፡፡ የጨዋታውን ውጤት በጋዜጦች ያነበቡት የእንግሊዝ ደጋፊዎች የጨዋታውን ውጤት የዘገበው ጋዜጣ ተሳስቶ እንጂ እውነት ሳይመስላቸው አልፎአል፡፡
Posted on: Thu, 29 May 2014 08:24:21 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015