ECX’s CEO Resigns | የኢትዮጵያ ምርት ገበያ - TopicsExpress



          

ECX’s CEO Resigns | የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸው እውን እንደሆነ ተዘገበ። ከ5ቀናት በፊት ድሬቲዩብ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንተነህ አሰፋ የስራ መልቀቀዊያ በማስገባት ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ምንም እንኳ ዋና ስራ አስፈጻሚው ከሃገር ከወጡ ቆየት ያሉ ቢሆንም ወሬው አሁን ነፍስ ዘርቶ ነው በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እየተዘገበ ይገኛል። ሪፖርተር ጋዜጣ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው አቶ አንተነህ ከኃላፊነት የለቀቁት አሜሪካ ሆነው ባመለከቱት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ሲሆን፣ የምርት ገበያው ቦርድ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አፅድቆታል፡፡ በቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሰ ሊቀመንበርነት የሚመራው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቦርድ የሥራ መልቀቂያውን ተቀብሎ ውሳኔ የሰጠው፣ ሐሙስ መጋቢት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. መሆኑን የተገኘው መረጃ እንደሚያሳይም ተዘግቧል፡፡ አቶ አንተነህ ሥራቸውን ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ ያደረሳቸው የጤና ችግር መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በልብ ሕመም ምክንያት በአገር ውስጥ በሕክምና ላይ እንደነበሩና አነስተኛ ቀዶ ጥገና ተደርጐላቸው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ በዚህ ምክንያት ለከፍተኛ ሕክምና አሜሪካ የሄዱት አቶ አንተነህ፣ ሕክምናውን እዚያው በቅርብ እንዲከታተሉ በመወሰኑ ሥራቸውን ለመልቀቅ እንደተገደዱ እየተነገረ ነው፡፡ ወደ አሜሪካም ሲጓዙ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው እንደሆነም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎችን ጠቅሶ ሪፖርተር ጠቁሟል፡፡ በሥራ ገበታቸው ላይ ሳይገኙ ከሁለት ወራት በላይ የቆዩት አቶ አንተነህ፣ ይመለሳሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ጊዜ የሥራ መልቀቂያ መላካቸው ያልተጠበቀ ነው መባሉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ለተጨማሪ…. diretu.be/873479
Posted on: Sun, 16 Mar 2014 16:30:00 +0000

Trending Topics



words about a downhill
Hoy Amigos campechanos acaban de agredir a nuestras vompañeras
When I look at my babies, no matter how big they get, I know I

Recently Viewed Topics




© 2015