Pioneer Cement Factory Workers Returned to Work after a One Day - TopicsExpress



          

Pioneer Cement Factory Workers Returned to Work after a One Day strike ...See at... diretu.be/387876 | የፓዮኔር ስሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች ከአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ በኋላ ስራቸውን ጀመሩ፡፡ ከድሬዳዋ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው እና ከ5 ዓመታት በፊት በቻይዊ ባለሃብት የተቋቋመው የስሚንቶ ፋብሪካው ሰራተኞች ሊሟሉ ይገባቸዋል ያሏቸው ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው ትላንት ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም ስራ ለማቆም እንደተገደዱ ተናግረዋል፡፡ የፋብሪካው ሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ ስንታየው ታደሰ ለድሬቲዩብ እንደተናገሩት ሰራተኞቹ በስራ ላይ የሚያጋጥሟቸውን የተለያዩ ችግሮች በተመለከተ ከማንጅመንቱ ጋር ቀርበው ለመነጋገር ቢሞክሩም ቀና ምላሽ ማግኘት አልቻሉም፡፡ በአሳት ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች ለተደጋጋሚ አስከፊ የጤና መቃወስ እየተዳረጉ መምጣታቸውን ተከትሎ ያነሱት የ‹‹ደሞዝ ይጨመረልን ›› ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱ ደረጃ በደረጃ ወደ ሁሉም የፋብሪካው ሰራተኞች ጥያቄነት እንደተለወጠ አቶ ስንታየሁ እና ያነጋገርናቸው የፋብካው ሰራተኞች ገልጸውልናል፡፡ የፋብሪካው ሰራተኛ ወደ ስራ ገበታው ሊመለስ የቻለው የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ጸሃፊ፣ የምስራቅ ኢሰማኮ ቅ/ጽቤት ሃላፊ እንዲሁም የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ከሰራተኞች ተወካዮች እና ከማኔጅመንቱ ሃላፊዎች ጋር ከመከሩ በኋላ መሆኑን የሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር ገልጸውልናል፡፡ ነገ ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም ለመወያየት ቀጠሮ የያዙት የከተማው ባለስልጣናት ፣ የሰራተኞቹ ተወካዮች እና ማኔጅመንቱ ከሰራተኞቹ በኩል ሊሟሉ ይገባል በተባሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ተገልጿል፡፡ ሰራተኞች በዋናነት ያቀረቡት ጥያቄ የደሞዝ፣ የህክምና ፣የንጹህ የመጠጥ ውሃ ፣ የበርሀ አበል እና የስራ ላይ ደህንነት ጥያቄዎችን መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ሰራተኞቹ በዓመት የሚጨመርላቸው ደሞዝ ከአንድ ብር እስከ አምስት ብር ብቻ መሆኑን ፤ በፋብሪካው ውስጥ ያለው የህክምና መስጫ የጤና ቢሮ የማያውቀው እና ሃኪሙም ቻይናዊ በመሆኑ በቋቋንቋ መግባባት ካለመቻላቸው በተጨማሪ የሚታዘዙላቸው መድሃኒቶች የአጠቃቀም መመሪያቸው በቻይንኛ መሆናቸው ችግር እንደፈጠረባቸው፤ በህግ የተፈቀደላቸው የበረሃ አበል ተከፍሏቸው እንደማያውቅ እንዲሁም ለስራ ደህነነት የሚውሉ የደህንነት ኮፍያዎች ፣ጫማዎች ፣የአየር ማጽጃዎች እና ሌሎች መገልገያዎች ያልተሟሉላቸው መሆኑን በመጥቀስ ይህ እንዲሟላላቸው ጠይቀዋል፡፡ የሰራተኞቹ ተወካይ ፋብሪካው ምላሻችንን መስማት ካልቻለ ሙሉ በሙሉ ህጋዊ መስመር ይዘንና ከስራ ገበታችን ሳንርቅ ለሰራተኛ እና አሰሪ ቦርድ እና ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ጉዳያችንን እናቀርባለን ብለዋል፡፡
Posted on: Mon, 28 Apr 2014 18:30:00 +0000

Trending Topics



ass="stbody" style="min-height:30px;">
Hola a todos, aquí Jafu53, les comento que el servidor se
On this the day of June 27, 2013, @ 9:25pm mountain standard time.
MKJ Daycare is a safe, secure and nurturing environment for
New broadcast of Answers From the Book today on wogaradio at 3:00

Recently Viewed Topics




© 2015