ፖለቲካ በፈገግታ “የኢቴቪዋ ኦሮሚያ” - TopicsExpress



          

ፖለቲካ በፈገግታ “የኢቴቪዋ ኦሮሚያ” ናፈቀችኝ! ማርና ወተት የሚፈልቅባት ፣ የመብራት ... የውሃ... የኔትዎርክ ... የትራንስፖርት ችግር የሌለባት ፣ በኑሮ ውድነት ህዝቦቿ የማይማረሩባት ፣ ዜጎቿ ድህነትን በመሸሽ ወደ ማያውቁት አረብ አገር የማይሰደዱባት (ምን አጣን ብለው!) ፣ የመልካም አስተዳደር እጦት ከናካቴው የሌለባት ፣ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸዉ የማይባረሩባት፤ ምሁራኖቿ የማይሳደድቧት የማይታሰርቧት፤ ጀግኖቿ አሸባሪ እየተባሉ የማይረሸኑባት ፤ መብትን ማስከበር የሚቻልባት ኦሮሞነትን እንደ ዘረኝነት የማይቆጠርባት፤ ገበሬዎች ሚሊየነር የሆኑባትና ሁሉ ነገር ሞልቶ የተረፈባት “የኢቴቪዋ ኦሮሚያ” ናፍቃኛለች! (እናንተስ?)
Posted on: Sat, 21 Sep 2013 21:49:50 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015